Arba Minch Agricultural Research Center

Addis Zemen Tahsas 9, 2013

ለመጀመሪያ ዙር የወጣ

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ //ኢንስቲትዩት /ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል የኩልፎ ወንዝ ጎርፍ ማገጃ ግንባታ ሥራ 2013 በጀት ዓመት በግልፅ ጨረታ በግንባታ ሥራ በተደራጁ ማህበራት አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁመሠረት፡-

  1. ደረጃቸው BC/GC 9 ጀማሪ ጥቃቅን የተደራጁ ማህበራት ሆነው በኮንስትራክሽን መምሪያ በክልሉ ኮንስትራክሽን ቢሮ 2010 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ወይም የብቃት ማረጋገጫ ያሳደሱ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ TIN Number ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣  የአደረጃጀት መረጃ እና የአቅራቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም 2012 በጀት ዓመት ግብር የከፈሉና ከሊራንስ ከገቢዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ያልተሟላ መረጃ ማቅረብ ከጨረታ ያሠርዛል፡፡ ማንኛውም ተጫራች ባለፉት ሦስት ዓመታት ማለትም 20102011 እና 2012 . ውል ገብተው የግንባታ ሥራከጀመሩ በኋላ ያላቋረጡ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ከዞን ኮን/ሽን መምሪያ (/ቤት) መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎችንና መሣሪዎችን በግላቸው አጓጉዘው የሚሰሩ መሆን አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ 20000 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያውን በፖስታ በማሸግ ኦርጅናል /ዋናውን/ ፋይናንሻል ሠነድ ውስጥ ማስገባት አለበት።
  4. ተጫራቾች ህጋዊ ፈቃዳቸውንና ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ የተመዘገቡበትን ሠርተፊኬት በማቅረብ የጨረታውን ዱክሜንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስተው እስከ 21 ተከታታ ቀናት የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ ብር/ /ምንጭ ግብርና ምርም ማዕከል ///ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የከፈሉበትን ወይም  ገቢ ያደረጉበትን ስሊፕ በማቅረብ የጨረታው ሠነድ ከሥራ ሂደቱ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ከውድድሩ በፊት የሥራ ሣይቱን በራሱ ወጪ አይቶ ስለ ሣይቱ በማረጋገጥ ነጠላ ዋጋ መሙላት አለበት። እንዲሁም የሣይት ፎቶና የአሠሪው /ቤት ማረጋገጫ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ መረጃውን ያላቀረበ ከጨረታ ሠረዛል፡፡
  6. የፋይናንሻል ጨረታ በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ ተጽፎበት በሁሉም ፖስታዎች ላይ ሥም፣ አድራሻና የፕሮጀከቱ ሥም በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም የጨረታ ሠነድ ኦርጅናል በአንድ ፖስታ ከላይ በተገለፀው በተመሣሣይ ሁኔታ በሰም በታሸገ ኣንድ ትልቅ /እናት/ ፖስታ ውስጥ ከተውና ከላይ የተገለፁት ዝርዝሮች ሁሉ ተጽፎበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 22ኛው ቀን ከጧቱ 400 ሰዓት /ምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል /ፋን/ ሥራ ሂደት በቢሮ ቁጥር 4 ለዚህ በተዘጋጁ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። አንድ ኦርጅናል አንድ ፎቶ ኮፒ የህጋዊነት ማረጋገጫ መረጃ በአንድ እናት ፖስታ ተደርጎ መቅረብ አለበት።
  7.  የጨረታው ሣጥን በተገለፀውቀንና ከጧቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚህ ዕለት ከቀኑ 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ታሽጎ በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል።
  8.  የማንኛውም ተጫራች አርትሜቲክ ቼክ ውጤት ከተነበበው ዋጋ አንፃር 2% በላይ እና በታች ሆኖ ከተገኘ ከጨረታ ውጪ ይሆናል። በተመሣሣይ ቅናሽ 10% በላይ ማድረግም ከጨረታ ውጪ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
  9. ዋጋ መስበርም ሆነ መቆለል እንዲሁም ያልተመጣጠነ ዋጋ የሚያቀርብ ተጫራች የዋጋ ትንተና ግዴታ ያለበት ሲሆን፤ የዋጋ ትንተናውን ከባለሙያ ግምት ጋር ተነጻጽሮ ከገበያ ዋጋ ዝቅ ያለ መሆኑ ሲረጋገጥ የጨረታ ህግ ተከትሎ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ነገር ግን እቃ የማይገዛና ሆን ብሎ ዋጋ ዝቅ በማድረግ ጨረታ ለማሸነፍ በሚል ነጠላ ዋጋ  ማቅረባቸው ሲረጋገጥ ከጨረታው ይሠረዛል፡፡
  10. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው። በተጨማሪም የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

 

ስልክ 0468813331 / 0916552271/ 0910701082

በደ/////መንግሥት በደቡብ

ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

የአርባምንጭ ግብርና ምርምር ማዕከል