Welkite City Administration

Addis Zemen ግንቦት26፣2012

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው ዓይነት፡- የኮብል እስቶን ግንባታ የጨረታ መለያ ቁጥር-011/2012

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት ጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ ቤት ለወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚውል ማለትም፡- የዲች ግንባታ ለማሰራት ሕጋዊ መልክ ተደራጅተው ከሚገኙና መልካም አፈፃፀም ካላቸው በዘርፉ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው በጥቃቅንና አነስተኛ በተደራጁ የኮንስትራክሽን ማህበራት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

 • ሎት 1 ከጃቢር መስጅድ እስከ ኮብል ስቶን ኳሩ ሳያት 01
 • ሎት 2 ከጃቢር መስጅድ እስከ ኮብል ስቶን ኳሪ ሳይት 02
 • ሎት 3 ከመሀመድ ቤት እስከ ጎርጅ ሎት 03 

በዚህም መሠረት፡- ከዚህ በታች የተገለጹት መስፈርቶች የሚያሟሉ የኮንስትራክሽን ማህበራት በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡ 

 • 1ኛ/ ከወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት በውድድሩ እንድትሳተፉ የሚያስችላችሁ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የምትችሉ ማህበራት፡፡
 • 2ኛ/ ሕጋዊና የታደሰ የሥራ ፍቃድ ኖሯችሁ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈላችሁ፣ ቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆናችሁና የቫት ሰርተፊኬት ያላችሁ ማህበራት እንዲሁም የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ ተወዳዳሪዎች፡፡
 • 3ኛ የተረከባችሁትን ሥራ ለመስራት የሚከፈላችሁ ገንዘብ ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ወልቂጤ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በኩል ለመውሰድ የምትችሉ፡፡
 • 4ኛ/ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 
 • 5/ ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) ኣዲስ ክ/ከተማ ከሚገኘው የገቢዎች ቅርንጫፍ ቢሮ በመከፈልና ሪሲቱን በመያዝ ከወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 • 6ኛ/ በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ስም የተሰራ ለሦስቱም ሎት ለእያንዳንዱ በተመሳሳይ የ5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ወልቂጤ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ተወዳዳሪዎች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ ሲያስገቡ ሲፒኦ ኮፒ በማድረግ ከኦርጅናል ጋር በተጨማሪነት አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • 7ኛ| ተወዳዳሪዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብታቸው በማሸግ በእናት ፖስታ አድርጎ በማሸግ ወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ዋና/ሥራ/ሂደት ክፍል ውስጥ ለዚሁጨረታተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • 8ኛ መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ማሳሰቢያ፡

 1.  ማንኛውም ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ከዋጋ ጥናት መረጃ ጋር 15% ከፍ የሚል ከሆነ ውድቅ ይደረጋል፡፡ 
 2. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ኮሚቴ ጨረታው ሊከፍት ይችላል፡፡ 
 3. በ2012 በጀት ዓመት ሥራ ያገኘ፣ ሌላ ሥራ አሸንፎ ያልጨረሰና የአፈፃፀም ችግር ያለበት ማህበር በጨረታው መወዳደር አይችልም:: 
 4. አንድ ተወዳዳሪ መወዳደር የሚችለው በአንድ ሎት ላይ ብቻ ነው:: 
 5. በተደረገው የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ (Artimetic Error) የመጣው ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የተወዳዳሪው ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡ 
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ አግባብነት የሌለው ከሆነ ኮስት ብሬክ ዳወን የምንጠይቅ መሆኑ፡፡ 
 7. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡ 
 8. ተጫራቶች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው በሁሉም ገጽ እና ፖስታ ላይስማቸው፣ ፊርማቸውና ማህተም ማሳረፍ አለባቸው፡፡ መወዳደር 
 9. መ/ቤቱ ከሸጠው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ ሞልቶ አይቻልም፡፡ 
 10. የ70/30 ፍቃድ የታደሰውን ተጫራቾች ከጨረታ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንታቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 11. በጨረታ ሰነድ ሽያጭ ወቅት ቢሮ አካባቢ በመሆን የጨረታውን ሂደት የሚያውክ ሥራ የሚሰራ ማለትም ይህ ሳይት የኔ ነው ብሎ ሌሎች ተወዳዳሪዎችን በቼን ወይም በብር የሚደልል ተወዳዳሪ ከተደረሰበት እንደ አስፈላጊነቱ የጨረታ ሳይት የምንሰርዝ መሆኑና መመሪያው የሚፈቅደውን እርምጃ የምንወስድ መሆኑ፡፡ 

ለበለጠ መረጃ አድራሻ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት ብሩክ ሕንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ ውስጥ ኛ ፎቅ ወደቀኝ ሲታጠፉ የወ/ካ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0113301548/0113302547 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡ 

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ያፋ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት