Yeka sub City Administration woreda 04 finance office

Addis Zemen ጥቅምት24፣2013

የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 04 ፋይናንስ/ጽ/ቤት የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/በ2013 በጀት አመት

 • የተለያዩ የቢሮ መገልገያ አላቂ እቃዎችንና
 • የደንብ ልብስ፣
 • የጽዳት ዕቃዎች፣
 • የስፖርት ትጥቅ፣
 • ቋሚ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከጨረታ ስመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ ::

 1. ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ እና አገልግሎቶች አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
 3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆናቸውን
 4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድን ዋና እና ኮፒ በማዘጋጀት በታሸገ ኢንቨሎፕ በአንድ ወይም ከሁለት ወጥ ፖስታዎች (ቴክኒክ) የሚወዳደርበትን አይነት በፖስታው ላይ በመለየት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
 5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለሚጫረቱበት አይነት የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክ/ከተማ በወረዳ 04 ፋይናንስ /ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ቢድ ቦንድ ብር 2000( ሁለት ሺህ ብር ) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ /ሲፒኦ/ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
 7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ የምታስገቡ ሆኖ በአስራ አንደኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በእለቱ ተጫራቶች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ወጣት ማዕከል ሶስተኛ ፎቅ ከቀኑ 8:30 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የቢሮ መገልገያ እቃዎች ቅድሚያ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
 9. ተጫራቾች በማያቀርቡበት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውንና ማህተም፣ ፊርማ፣ አድራሻቸውን ማስቀመጥ አለባቸው
 10. የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ባሸነፋት እቃ ዋስትና ውል ማስረከቢያ 10% በማቅረብ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርበታል፡፡
 11. ጨረታውን ለማሳሳት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንዲሆኑና በወደፊት በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ ያስያዙትን የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ( ሲፒኦ) እንዲወረስ ይደረጋል፡፡
 12. ተጫራቾች ማጭበርበርና ሙስና (ጉቦ) ከመስጠት በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚከበር መሆኑን ማረጋገጥ
 13.  ተጫራቾች የዕቃ ዝርዝር ዋጋ ስታቀርቡ ከነቫቱ መሆኑን እያሳወቅን ከቫቱ ውጪ ያቀረበ ከውድድር ውጪ እንደሚሆን እናሳውቃለን፡፡
 14. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 60 ቀናቶች ይሆናሉ።
 15. መስሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ማሳሰቢያ፡-

 • ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0111261050 /0111261063 መደወል ይችላሉ ፤ በየካ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 04 ፋይናንስ/ጽ/ቤት ልዩ ቦታ ሚኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል በሬሳ በር 200 ሜትር ገባ ብሎ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየካ ክ/ከተማ የወረዳ

4 አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት