kara Kore Kindergarten and Primary School

Addis Zemen Tahsas 23, 2013

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ ወረዳ 03 በካራ ቆሬ እፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 2013 ዓም የስራ ዘመን የቢሮ መግልገያዎችና የተለያዩ እቃዎችን ማለትም

 • ሎት1  ቋሚ እቃ ኤሌክትሮኒክስ (6313)
 • ሎት2  የደንብ ልብሶች(6211)
 • ሎት3 የፅህፈት መሳሪያና ሊሎች(6212)
 • ሎት4 አላቂ የትምህርት እቃዎች (6215)
 • ሎትየተለያዩ መሳሪያዎች እና መፃህፍት(6219)
 • ሎት6 ሌሎች አላቂ እቃዎች (የፅዳት እቃዎች) (6218)
 • ሎት7 የህክምና እቃዎች(6214)
 • ሎት8 ቋሚ እቃዎች (6314)
 • ሎት9 ህትመት(6213)

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 1. የጨረታው ቁጥር 005/2013 ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡
 2. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር/supplierlist/ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ በባለስልጣኑ በመንግስት አካል የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉእና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50(ሀምሳ ብር ብቻ) በመከፈል ወትር በስራ ሰዓት በኮ/// ወረዳ 03 በካራ ቆሬ እፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግራር ባጃጅ መያዣ ከፍ ብሎ ኮንደሚኒየም እለፍ እንዳሉ ከመስቀሉ ፊት ለፊት በሚገኘው በካራ ቆሬ አፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ክ/ሂ አስተዳደር ቢሮ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10(አስር) ቀናት እሁድና ቅዳሜን ጨምሮ ከጥዋቱ 230-1130 ከምሳ ሰዓት ውጪ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. በጨረታ ሰነዱ ላይ ያለውን እቃ ናሙና ወይም ሳንፕል ማቅረብ ግዴታ መሆኑን እየገለጽን በአካል ማቅረብ የማይቻል ከሆነ በፎቶ ወይም ድርጅቱ ደረስ በመውሰድ ማሳየት ግዴታ አለባቸው :
 7. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም፡፡
 8. ገዥው በእካል የሚገዛውን እቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
 9.  ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን(ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል) ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 1130 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
 10.  ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ 430 ይከፈታል፡፡
 11. የሚቀርበው የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡
 12. ለአሸናፊተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ የተመለከተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን የእቃ ዋጋ 10% ገቢ አድርገው ውል መዋዋል እለባቸው ፡፡
 13.  መስሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት  ጋር እስከ 6ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 14.  በጨረታ ሰነድ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በጽሁፍ ከጨረታው መከፈቻ 2 ወይም 3 ቀን በፊት ማቅረብ ይቻላል፡፡
 15. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ቅሬታ ካላቸው በት/ቤቱ //// አስተዳደር እና /አገ/ደጋፊ የስራሂደት ቅሬታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡በደጋፊ የስራ ሂደቱ የማይፈታ ከሆነ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ፡፡ጨረታው ውጤት በተገለፀ በ15 ቀን (አምስት) ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ገዥው ከአሸናፊው ጋር ውል ይፈጽማል፡፡
 16. አሸናፊው ድርጅት የግዢውን ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናትው ውስጥ እቃውን ገቢማድረግ አለበት፡፡
 17. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
 18. ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት እንዲሁም ያሸነፉበትን እቃዎች /ቤቱ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው
 19. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡

 

አድራሻ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ካራ ቆሬ ግራር ኮንደሚንየም መስቀሉ ጋር ከወረዳ 03 ጤና ጣቢያ ወረድ ብሎ ይገኛል ፡፡

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር -0113-48-19-99-08-32-74-28

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ትምህርትና ስልጠና /ቤት የካራ ቆሬ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት