Ewkete Wegene kindergarten &elementary School

Addis Zemen ጥቅምት29፣2013

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ አስተዳደር ዕውቀቴ ወገኔ አጸደ ሕፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያገለግሉ

 • አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
 • የጽዳት እቃዎች፣
 • አላቂ የትምህርት መሳሪያዎች፣
 • የደንብ ልብስ፣ ለህንጻ፣
 • ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ እቃዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣
 • ህትመት እና ፕላንት ማሽነሪ እና የተለያዩ መሳሪዎች ጥገና ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በዘርፉ የተሰማራችሁ ሕጋዊ ነጋዴዎች በጨረታ አወዳድረን በጥራት እና በዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ከሆኑት ድርጅት ለመግዛት እንፈልጋለን።

 1.  ተጫራቾች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር እና በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን ማሥረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
 2. ተጫራቾች የ2012 ዓ/ም ግብር የከፈሉና ለ2013 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ መሆኑን የሚገልጽ አግባብነት ያለው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
 3. . ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በዕውቀቴ ወገኔ አጸደ ሕፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የግዥ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር )ብቻ ከፍለው መውሰድ ይኖርቦታል ። ነገር ግን ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆኑ ካደራጃቸው ወረዳ የጨረታ ማስከበሪያ ህጋዊ ደብዳቤ በማምጣት መወዳደር እንደሚችሉ እየገለጽን ሰነዱን በመውሰድ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ የዕቃዎችን ዝርዝር ዋጋ እና አይነት በመግለጽ የሰነዱን ፖስታ በማሸግ በቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው ሣጥን ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
 4. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጎዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጐ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል። (ተጫራቾች መስፈርቱን ካሟሉ ሌሎች ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል)
 5.  ተጫራቾች ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ተንተርሰው ዋጋ መስጠት አይችሉም ::
 6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ህጋዊ ማህተብ ያረፈበት መሆን ይኖርበታል ።
 7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ዋጋ የዕቃውን አይነት ብራንድ/ እቃው የተመረተበት ሀገር በግልጽ መጥቀስ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚቀርቡት እቃዎች ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ ሲፒኦ/ በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብረው፤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተቁ

የግዥው አይነት

ሎት

የጨረታ

ማስከበሪያ

1

አላቂ የቢሮ እቃዎች

ሎት1

3000.00

2

የፅዳት እቃዎች

ሎት2

4000.00

3

አላቂ የትምህርት መሳሪያዎች

ሎት3

2000.00

4

የደንብ ልብስ

ሎት4

3000.00

5

ለህንጻ ፣ለቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ እቃዎች

ሎት5

1000.00

6

አላቂ የህክምና እቃዎች

ሎት6

1000.00

7

ቋሚ እቃዎች

ሎት7

4000.00

8

 

ህትመት

ሎት8

1000.00

9

ፕላንት ፣ማሽነሪ እና የተለያዩ መሳሪዎች ጥገና

ሎት9

1000.00

 በአጠቃላይ 20,000 .00 ( ሃያ ሺህ ብር) በት/ቤቱ ስም በማሰራት ከጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው ወረዳ ህጋዊ የዋስትና ደብዳቤ በት/ቤቱ ስም ማለትም በዕውቀቴ ወገኔ አፀደ ህፃናት እና የመ/ደ/ት/ ቤት በሚል አጽፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም በተወዳደሩት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ለግዥ ፈፃሚው አካል ማስያዝ አለባቸው :: ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውሉ መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡና  ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው።

10. አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ካልተዋዋለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለሙግስት ገቢ ይደረጋል።

11. በጨረታው ያሸነፉ ተጫራቾች ላሸነፋቸው እቃዎች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ በመክፈል በዕውቀቴ ወገኔ አጸደ ህጻናት እና የመ/ደ/ት/ቤት ንብረት ክፍል በስራ ቀናት ጠዋት ከ3፡00-6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት ከ8፡00-10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።

12. ት/ቤቱ አሸናፊ ተጫራቾች ከተመረጡ በኋላ በሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20 ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብታቸው የተጠበቀ ነው።

13. ተጫራቾች በጨረታው የአፈፃጸም ሂደት ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ ቁጥር 649/ 2001 አንቀጽ 51፤53 እና 54 እንዲሁም በሙግስት ግዥ አዋጅ አፈጻጸም መመሪያ አንቀጽ 43 መሰረት አቤቱታ የማቅረብ መብታቸው እንደተጠበቀ ነው።

14. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. በጨረታው ሰነድ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ በአካል በመቅረብ ዕውቀቴ ወገኔ አጸደ ህፃናት የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 መጠየቅ ይችላሉ።

 • አድራሻ በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አጠና ተራ አካባቢ 8 ማዞሪያ ድልድይ ሥር
 • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 2 79 11 29/011 2 73 90 66 ደውለው ይጠይቁ
 • ዕውቀቴ ወገኔ አጸደ ሕፃናት አና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት