በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውል ደብል ፒካፕ (Double Cabin PICKUP) ኤክስትራ ካፕ ፒካፕ (PICKUP Extra cab) መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ፍርድ ቤት በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመሥሪያ ቤቱ አገልግሎት የሚውል ደብል ፒኮካፕ (Double Cabin PICKUP) ኤክስትራ ካፕ ፒካፕ (PICKUP Extra cab) መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ 

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዚህ ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ያለው የ2012 የታደሰ ፍቃድ የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡ 
  2. አሸናፊው ድርጅት ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በአስር ቀን ውስጥ ያሸነፋቸውን ዕቃዎች ኩዩ ወረዳ ፍርድ ቤት ማቅረብ የሚችል፡፡ 
  3. ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የያዘ ጋዜጣው ከወጣበት ጀምሮ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 8 መጥተው መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  4. ተጫራቶች መኪናውን የሚሸጡበትን ዋጋ የያዘ ዝርዝር የዋጋ በፖስታ በማሸግ ሚያዝያ 3 ቀን 2012 ዓ.ም እስከ 8:00 ሰዓት ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000 /አምስት ሺ / ብር በማስያዝ ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት ያስገባሉ፡፡ 
  5. ጨረታው ሚያዝያ 3 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው ፍርድ ቤት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡ 
  6. መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  7. በሌላ ሰው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ 
  8. ተጫራቾች ለሙያቸው ማረጋገጫ የስራ ልምድ እና የምስጋና ደብዳቤ ቢያቀርቡ ይመረጣል፡፡ 
  9. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0111311505 / 0111310043/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን የኩዩ 

ወረዳ ፍርድ ቤት