Jimma Zone Yemana Woreda FEDB

Addis Zemen ነሐሴ22፣2012

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 

በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በ2013 የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉ፡-

 • የጽሕፈት፣የፅዳት መሣሪዎች/አላቂ የጽሕፈት ቤት ዕቃዎች፣
 • የደንብ ልብሶች እና መጋረጃዎች፣ ቋሚ የመስሪያ ቤት መሣሪያዎች/
 • Furniture ፣ የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች፣
 • የኮቪድ 19 መከላከያ ዕቃዎች፣
 • የተለያዩ የህትመት ሥራ፣
 • የግንባታ እና የእድሳት ዕቃዎች፣
 • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የተለያዩ የሞተር ሳይክሎች እና
 • የመኪና (አምቡላንስ፣ ፒካፕ/ ኒሳን፣ ፓጃሮ ቪጎ) ጎማዎችን፣
 • የተለያዩ ሞተር ሳይክሎች፣
 • የሞተር ሳይክል ጋራዥ አገልግሎት እና ስፔርፓርቶች(መለዋወጫ) እና የተለያዩ የቴክኒከ እና ሞያ ማሰልጠኛ ዕቃዎችን ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ 

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እና ግዴታዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ 

የተጫራቾች መስፈርት/ግዴታዎች፡-

 1. ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡ 
 2. በመንግሥት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
 3. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የግዢ ደንብ እና መመሪያ የሚያከብር፡፡ 
 4. የ2012 ዓም ግብር የከፈሉ እና የ2013 ዓም የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ፍቃድ ያላቸው፡፡ የ2012ዓ.ም ግብር ያልከፈለ እና ለ2013 ንግድ ፈቃዳቸውን ያላደሱ ከሆነ ከገ/ባ/ጽ/ቤት ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡ 
 6. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያሳይ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የመጨረሻውን ወር የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያወራረደበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል። 
 7. ጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ለያንዳንዳቸው 5,000 (አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል ወይም ከተደራጁ 1 አንድ ዓመት ያልበለጡ ኢንተርፕራይዝ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል 
 8. ጽ/ቤቱ አስፈላጊ ነው ብሎ ባመነበት ዕቃላይ ተጫራቶቹ ናሙና እንዲያቀርቡለትማዘዝ ይችላል። 
 9. አሸናፊው ድርጅት ውል ከመፈራረሙ በፊት የሚገዙ ዕቃዎችን ናሙና በድርጅቱ ማህተም አስደገፈው ማቅረብ የሚችል፡፡ 
 10. የጨረታው ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከማ/ወ/ገ/ባ/ጽ/ቤት መግዛት የሚችል፡፡ 
 11. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ ማስገባት ይቻላል፡፡ 
 12. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በ5/1/2013 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በማስታወቂያ የተነገረ የመክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ 
 13. ረታው በተባለበት ቀን እና ሰዓት ገብቶ ካለቀ በኋላ በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት በማ/ወ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ 
 14. አሸናፊ ተጫራቾች ከጽ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም የሚችሉ እና የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በቼክ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት:: 
 15. አሸናፊው የተገዙ ዕቃዎችን ለማና ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጪ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
 16. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም:: 
 17. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ እና የማይነበቡ ነገር ሊኖር አይገባም፡፡ 
 18. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ በግልጽ ተለይቶ ሊቀመጥ ይገባል፡፡ የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መጨመሩን የሚገልጽ ጽሑፍ ከሌለ ጽ/ቤቱ ተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) እንደተጨመረበት አድርጎ ይወስዳል፡፡ 
 19. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 • ለተጨማሪ መረጃ፡-0472260016 / 0906246672/0932019433 ይደውሉ። 

በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት