SOUTH WEST SHEWA ZONE KERESANA MALIMA WEREDA FEDB

Addis Zemen ሐምሌ22፣2012

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የቀርሳና ማሊማ ወረዳ ገ/ኢ/ት /ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙት መንግስት መ/ቤቶች

 • የኤሌክትሮኒክስ፣
 • የጽህፈት መሳሪያዎችን፣
 • የህትመት መሳሪዎችን፣
 • የንጽህና መሳሪያዎችን ፣
 • አላቂ የቢሮ ውስጥ እቃዎችን ፣
 • የሠራተኛ የደንብ ልብሶችን
 • የቴክኒክና ሙያ መሰልጠኛ እቃዎችን፤
 • የግንባታ እቃዎችንና የተለያዩ ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች 
 1. እቃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ በ2013 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ 
 2. በገ/ኢ/ልማት ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ አካል በአቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፤
 3. ተወዳዳሪዎቹ መንግስት ባወጣው ህግ መሰረት የተጨማሪ እሴት ታክስ ( VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፤ 
 4. የግብር ከፋይነትና የአመቱን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርብ፤
 5. የውጭ ሀገር ተወዳዳሪ ከሆነ ከተቋቋመበት ሀገር የምስክር ወረቀት ወይም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት፡፡
 6. ተወዳዳሪው ከሙስናና ከማጭበርበር ተግባር የጸዳ ስለመሆኑና ሀገራዊና ክልላዊደንቦችን በማስከበር ጨረታውን ካሸነፈ ውሉን ለመፈረም የተዘጋጀ መሆን አለበት::
 7. ተወዳዳሪው በሚያቀርበው እቃ ዝርዝር የአምራች ሀገር ፣የእቃው ስም፣የሞዴል ቁጥርና የተመረተበት ዘመን ተዘርዝሮ መቅረብ አለበት፡፡
 8. / ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውምተወዳዳሪማሻሻያ ወይም ለውጥ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ መውጣት አይቻልም :: 
 9. ተወዳዳሪው የእቃ ናሙና በሙሉ ወይም በከፊል ሲጠየቅ እስከ ወረዳው ገ/ኢ/ት / ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ናሙና ማቅረብ የማይቻሉ እቃዎች የአምራች ሀገር፣የእቃው ስም፣የሞዴል ቁጥርና የተመረተበት ዘመን በመዘርዘር እንዲሁም የፎቶግራፋቸውን አልበም ማቅረብ አለበት፡፡ ለናሙና የቀረበውን እቃ አስፈላጊው ግምገማ ከተከናወነ በኋላ ለባለቤቱ ይመለሳል፡፡
 10. / ተጫራቾች በጨረታው ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በጥሬ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሰ፡፡ 
 11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመሰስ 150 ብር (አንድ መቶ ሃምሳ ብር ) በመክፈል በወረዳው ገ/ኢ/ት /ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 12.  የጨረታ ሰነዱን በአንድ በተዘጋጀ ኤንቬሎፕ በሰም በማሸግ በንግድ ድርጅቱ ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞና ማህተሙ አርፎበት መቅረብ አለበት::
 13. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግተው በዚህ እለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ሰአት ላይ በወረዳው ገ/ኢ/ል /ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡ 
 14.  ጨረታውን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ጨረታውን ማሸነፉ ተገልጾለት እስከ 5 ቀናት ድረስ ቀርቦ ዮግዥውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በገንዘብ በማስያዝ ውሉን መፈረም አለበት ያስያዙት ብር ተመላሽ የሚሆነው እቃውን ሙሉ በሙሉ ካቀረቡ በኋላ ይሆናል፡፡
 15.  ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣቀን አንስቶ እስከ 5(አምስት) ቀናት ማንኛውምተወዳዳሪ በጨረታው ሰነድ ላይ መግለጫ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ማቅረብ ይችላል፡፡ 
 16. ይህን ጨረታ ለማደናቀፍ የሚሞክር ተወዳዳሪ ከጨረታ ውጪ በመሆን ለወደፊትም መንግስት በሚያወጣው ጨረታ ላይ እንዳይካፈልና የጨረታ ማስከበሪያው የማይመለስበት ይሆናል፡፡ 
 17. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 18. / የጨረታው አሽናፊ እቃዎቹን እስከ ወረዳ ገ/ኢ/ት ጽ/ቤት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ 
 19. አድራሻችን ከአ/አበባ ወደ ቡታጅራ በሚወስደው መንገድ ላይ 60 ኪ/ሜትር ርቀት ላይ ሴመን ከተማ ይገኛል፡፡ 
 20. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 3630 321 ፣ 0926183695፣09 10 41 15 87 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

በደቡብ ምዕራብ ሽዋ ዞን ቀርሳና ማሲማ ወረዳ ገ/ኢ/ት /ጽ/ቤት