Gumbichu Wereda FEDB

Addis Zemen ሐምሌ25፣2012

የጨረታ ማስታወቂያ 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሸዋ ዞን መስተዳደር በጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለ2013 የበጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር መ/ቤቶች የሚያገለግሉ

 • የተለያዩ የግንባታ መሳሪያዎች ፣
 • የጽህፈት መሳሪያዎች ፣
 • የጽዳት ዕቃዎች ፤
 • አላቂና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ፤
 • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፤
 • የሞተር ጎማ ፤ ከማነዳሪ እና
 • የተለያዩ ለቴክኒክና ሙያ ት/ት ቤት የሚያገለግሉ ዕቃዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሠረት፡-

ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡ 

 1. ተጫራቶች ጨረታውን ለመካፈል ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 
 2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ብቻ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው ሆኖ ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና በፌዴራል ገ/ትብብር ልማት ቢሮ በአቅራቢነት ዌብ ሳይት ላይ ተመዝግበው ያሉ እና በአሁኑ ወቅት ዌብ ሳይት ላይ መገኘታቸውን የሚያመለክት ኮፒ ማስያዝ የሚችሉ ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 3. ተጫራቾች የሚጫረቱትን የዕቃ እስፔስፊኬሽን ሙሉ በሙሉ መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን በም/ሸ/ዞንበጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብና ትብብር ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 5. ማንኛውም ተጫራች ከሚያቀርበው ዋጋ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጥቃቅንና አነስተኛ ወይም ማይክሮ ከሆኑ ካደራጃቸው አካል የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 6. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 
 7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ መ/ቤቱ ድረስ በመምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡ 
 8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 • አድራሻ፡ ከአዲስ አበባ በሰንዳፋ 65 ኪ.ሜ ሲሆን በቢሾፍቱ በኩል 82 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- የቢሮ፤- 022 4510008/0912230467/0912828572 መደወል ይችላሉ፡፡ 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሸዋ 

ዞን መስተዳደር በጉምቢቹ ወረዳ ገንዘብና 

ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት