Oromia Regional Government Buildings Management Bureau Adama District

Addis Zemen Tir 11, 2013

ለ2ኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት አዳማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት (ገልማ አባ ገዳ የስብሰባ ማዕከል) ከዚህ በታች በሎት ተለይተው የተዘረዘሩትን

 • የአየር ማቀዝቀዣ ሲስተም (Air Cooling System) እቃዎችን፤
 • የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎችን፤
 • ICT እቃዎችን፤
 • የጄኔሬተር ጥገና መለዋወጫ እቃዎችን በንግድ ዘርፉ የተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጅቶች፣ማህበራትና ግለሰቦች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል (ጥሪ ያደርጋል)፡፡

በዚህ መሠረት

 • ሎት 1 የአየር ማቀዝቀዣ ሲስተም (Air Cooling System) እቃዎችን፣
 • ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስና ኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎችን፣
 • ሎት 3 የICT እቃዎች እና መለዋወጫዎችን፣
 • ሎት 4 የጄኔሬተር ጥገና መለዋወጫ እቃዎችን፣

ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚጠበቅባቸው ተፈላጊ መስፈርቶች፡

 1. ተጫራቾች በጨረታ ለመካፈል ህጋዊ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር (TIN Number) እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ከላይ በተገለጹት ሎቶች የንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 3. እንስቶል መሆን በሚገባቸው የእቃ ዓይነቶች ላይ የምትወዳደሩ ድርጅቶች የምትሰጡት ዋጋ የእቃውን እና የኢንስቶል ማድረጊያ ዋጋ ጭምር አካቶ መሆን ይኖርበታል፡፡
 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ የመንግሥት ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት አዳማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት (ገልማ አባ ገዳ የስብሰባ ማዕከል) 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 የማይመለስ ብር 50.00 (ሃምሳ) መክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
 5. በሎት 1 ላይ የምትወዳደሩ ተጫራቶች ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) እና በሌሎች ሎቶች ላይ የምትወዳደሩ ድርጅቶች ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያው (CPO ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታው የተሸነፉት ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያው (CPO) ተመላሽ ይሆናል፡፡
 6. ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ይሸጥና በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) የሥራ ቀን ከ2፡30 እስከ 8፡00 ሠዓት ድረስ ለጨረታ ሠነዱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ማለትም በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም በጨረታው ለመካፈል የፈለጉ ማናቸውም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጫራቾች አለመገኘታቸው ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
 7.  ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱ ማህተም አርፎበት መ/ቤቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በጨረታው የመክፈቻ ዕለት ማስገባት አለባቸው፡፡
 8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ እና ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
 9. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ 10/100 በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ፤ አለበት፡፡
 10. የውል ማስከበሪያውም አሸናፊው ድርጅት እቃዎቹን በሙሉ የጊዜ ገደብ ጨርሶና አስገብቶ እስኪያጠናቅቅ ድረስ ተይዞ የሚቆይ ይሆናል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ እንስቶል መደረግ ያለበት እቃ እንስቶል ሆኖ መሥራቱ እስኪረጋገጥ ድረስ የውል ማስከበሪያው ተይዞ የሚቆይ ይሆናል፡፡
 11. ለጨረታው የሚቀርበው ሠነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በግልፅ ተጽፎ የድርጅቱ ማህተም በጨረታ ሰነዱ (በዋጋ መሙያው) ላይ ጭምር አርፎበት (ተመቶበት) መቅረብ አለበት፡፡
 12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ውጤት በውስጥ ማስታወቂያ ቦርድ ላይ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ5 (አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታው ውጤት ላይ ቅሬታ ካለው ቅሬታውን ለጽ/ቤቱ በጽሑፍ ማቅረብ ይችላል፡፡
 13. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሠነዱ ላይ ያቀረበው ዋጋ ያሽነፈበት እቃ ገቢ ሆኖ እስከሚጠናቀቅበት እና እንስቶል መሆን የሚገባው እንስቶል ሆኖ አስኪጠናቀቅ ደረስ ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
 14. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ቫት ማካተት አለ ማካተቱን መግለጽ የሚኖርባቸው ሆኖ የማይገልጽ ድርጅት ካለ ግን የሰጠው ዋጋ ቫትን አካቶ እንደሆነ ታሳቢ ተደርጎ የሚወዳደር ይሆናል፡፡
 15. ማንኛውም ድርጅት የሚወዳደርባቸውን እቃዎች ሳምፕል እና ከመወዳደሪያው ዋጋ ጋር ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ ካልሆነ ከውድድር ውጪ የሚሆን ይሆናል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ መቅረብ እንደማይችሉ የሚታመንባቸው (ከውጭ) ሃገር የሚገቡ የእቃ ዓይነቶች ብቻ ስለእቃው የሚገልጽ ፎቶግራፍ ሲያቀርብ ተቀባይነት ሊኖረው ይችላል፡፡
 16. ማንኛውም ተወዳዳሪ የተጠየቀውን መስፈርት ሳያሟላ የተወዳደረ እና ሳምፕል ናሙና ያላቀረበ ከውድድር ውጪ የሚደረግ ይሆናል፡፡
 17. መስሪያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡

 • ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን ሙሉ እስፔሲፊኬሽን በጥሞና አረጋግጦ መረዳት ይኖርበታል፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ ለሚፈጠረው ስህተት ምንም አይነት ማስተካከያ የማናካሂድ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡
 • በተጨማሪም በተሠጠው እስፔሲፊኬሽን ላይ ምንም ዓይነት ማስተካከያ ማድረግ አይቻልም፡፡
 • ውድድሩን ያሸነፉ ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጭነው አዳማ ገልማ አባ ገዳ የስብሰባ ማዕከል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተወዳዳሪ ድርጅቶች ሁሉ በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተጠቀሱ ከሁሉም የሥራ መስክ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የፌዴራል እና የክልሉ የግዢ ህጎችን ጭምር የማክበር ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡
 • ተጫራቾች በአማራጭነት ማቅረብ እንደሚችሉ ከተጠየቁት የእቃ ዓይነቶች በስተቀር በሌሎች የእቃ ዓይነቶች ላይ በተጠየቀው እስፔስፊኬሽን እና በጨረታ ሰነዱ ላይ እንጂ በአማራጭ እና በተጫራቹ የዋጋ ማሳወቂያ ሰነድ ላይ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

አድራሻ፡አዳማ ከተማ መግቢያ ከረዩ ሆቴል ፊት ለፊት ገልማ አባ ገዳ የስብሰባ ማዕከል ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው፡፡

ስልክ፡- 022-212-03-81, 0912051357፤ 0912110110 ደውለው አስፈላጊውን መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ሕንፃዎች አስተዳደር ድርጅት

 አዳማ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት