Shashemene City Water Supply & Sewerage Service

Addis Zemen Tir 19, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሻሸመኔ ከተማ መስተዳድር የሻሸመኔ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የውሃ ቆጣሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራች እንዲወዳደሩ ይጋበዛሉ፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች –

 1. እቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያድሱ መሆን አለባቸው :
 2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ 1% ሲፒኦ ወይም በቼክ ከሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር ማስያገ/ እለባቸው
 3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመከፈል ከሻሸመኔ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ አስተዳደርና ሎጀስቲክ ከፍል በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ::
 4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን በመከተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል:
 5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 6:00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወደ ም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ጋር መሆኑን ወይም አለመሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው እሸናፊው ድርጅት በፅሑፍ ከተገለፀ በኋላ ይሆናል፡፡
 8. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተሰጠው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሑፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ በሻሸመኔ ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ውል መፈራም አለበት-ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
 9. የእቃዎች ረከብ የሚካሄደው በሻሸመኔ ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎትጽርጅት ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡
 10. . የእቃው ብዛት(Quantity) የሚወሰነው በመስሪያ ቤቱ (በድርጅቱ) የበጀት ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ ነው
 11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራፎች ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ሆኖ ከበጀታቸን በላይ የሚሆነውን መቀነስ ወይንም የምችል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

2 ተጫራቾች መመሪያ

2.1 የዘመኑን ግብር ከፍሉ ማጠናቀቁን የሀገር ውስጥ ገቢ መሥሪያ ቤት ማስረጃ በእጅ ማቅረብ አለበት

22ተጫራቾች እቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን ይኖርበታል:

23 ተጫራች የዘርፉን የንግድ ፍቃድ ኦርጅናሉንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለበት።

2.4  ተጫራች የንግድ ፍቃዱ ከሚፈቅድለት ዘርፍ ውጪ መጫረት አይችልም።

2.5 በዋጋ አጻጻፍ ተራ ላይ ስር ድልዝ ካለ የተደለዘው (የተሰረዘው) ዋጋ ተቀባይነት የለውም (እይኖረውም፡፡

26 በእርሳስ እና ቀለም በሚጠጣ ብዕር እንዲሁም ከተሰጠው ቦታ ውጪ የተጻፈ ዋጋ ተቀባይነት የለውም (እይኖረውም)፡፡

2.7 የተጫራቹ ሙሉ ስም ፊርማ የድርጅቱ ቲተርና ማህተም የሌለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

2.8 አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ የማጓጓጓዣ ወጪ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል::

2.9 አሸናፊ ተጫራች የእቃዎቹን ናሙና ሲፈለግ አቅርቦ ማሳየት አለበት።

2.10 ተጫራቹ የእቃዎቹን ነጠላ ዋጋ በማያሻማ ሁኔታ ከመግለጽ ውጪ እንዲሁም ከተሰጠት የእቃ ስም ዝርዝሮችም ሆነ የእቃዎቹን መለኪያዎች ለውጥ (ቀይሮ) መጻፍ አይቻልም።

2.11 ተጫራቹ የእቃዎቹን ዋጋ ከዚህ ሠነድ ውጪ በለላ ዋጋ መስጫ ላይ ሞልቶ መመለስ አይችልም::

2.12 ተጫራቹ የሀገሪቱን የፈዴራልና የክልሉን አዋጆችና ደንቦችን የማክበርና ማታ አቅርቦት ወቅት የሚቀርበውን የውል ሰነድ መፈረም ይኖርበታል

2.13 ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረበው ዋጋ የማሻሻያ ሃሳብ ማቅረብና ራሱን ከጨረታው ማግለል አይችልም

2.14 አሸናፊ ተጫራች ከእያንዳንዱ እቃ የሰጠው ነጠላ ዋጋ እስከ 30/10/2013 ዓ.ም ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን አውቆ ጽ/ቤቱ ተጨማሪ የግዢ ጥያቄ ፍላጎት ባቀረበበት ወቅት ለማቅረብ ፍላጎት ያለውና ለማቅረብ ውል መፈፀም የሚችል መሆን አለበት::

2.15 አሸናፊ ተጫራች ጽ/ቤቱ ከሚያደርገው የግዢ ውል 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት የሚችል መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል፡፡

2.16 አሸናፊ ተጫራች ክፍያ የሚፈፅምለት እቃዎቹን ገቢ አድርጐ ሲያጠናቅቅ ይሆናል፡፡

2.17 ተጫራች በማንኛውም ሁኔታ የጨረታውን አካሄድ ሥነ-ሥርዓት ለማስቀየርም ሆነ ለማሣሣት ከሞከረ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዝነው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ተደርጐ ወደ ፊት በሚወጣው የጨረታ ማስታወቂያ ላይ እንዳይሣተፍ ይደረጋል::

2.18 ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርባቸው የእቃ ዋጋዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ማካተቱንና አለማካተቱን መግለጽ ይኖርበታል፡፡

2.19 መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የተጫራቹ ስም

ፊርማ አድራሻ-የተጫራች የድርጅቱ ማህተም

አድራሻ፡- የሻሸመኔ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

ስልክ ቁጥር፡- 046 110 2093 / 0916581638 /0916002432

0991320212/091 6871624

የሻሸመኔ ከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት  ድርጅት