• Oromia

Oromia Regional State Urban Development and Construction

Addis Zemen ጥቅምት21፣2013

የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር – ኦከልቤቢ አቃና አገልግሎት 1/2013

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ለ2013 በጀት ዓመት የሚውል፡

 1. ሎት 1- የጽህፈት መሳሪያዎችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
 2. ሎት 2 -የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች
 3. ሎት 3- የሲሲቲቪ ካሜራ አቅርቦትና ገጠማ ሥራ
 4. ሎት 4-የተለያዩ የመኪና ውበት መጠበቂያ ዕቃዎች
 5. ሎት 5- የአበባ ችግኝ፣ ግብዓት አቅርቦትና ማስዋብ ሥራ
 6. ሎት 6 – ገጭ ማሳያዎች (ኤሌክትሮኒክስ ቦርድ፣ ቢልቦርድ፣ ኢሚቴሽን፣ ስክስሪክ ማይኮችንና ሌሎች ህትመት ነክ ሥራ) ስመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:

 1. ለተጠየቁት የግዢ ዕቃዎች የዘርፉን ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የ2013 ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ በፌዴራል ወይም በክልል የገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት መስሪያ ቤት በአቅራቢነት የተመዘገቡ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ዋናውንና ኮፒዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢዉ መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸውና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ለእያንዳንዱ ዘርፍ ብር 50.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሳር ቤት ኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ 1ኛ ፎቅ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመሙላት ለእያንዳንዱ ዘርፍ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ 1ኛ ፎቅ ግዢና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዘወትር በሥራ ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታውም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን (ዕለቱ በዓል ወይንም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ቢሮ 1ኛ ፎቅ ግዢና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡፡
 5. ማንኛውም ተጫራች በኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ስም ከታወቀ ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1ብር 5,000.00፣ ለሎት-2 ብር 1,500.00፣ ለሎት-3 ብር 10,000.00፣ ለሎት-4 ብር 4000.00፣ ለሎት-5ብር 5,000.00 እንዲሁም ለሎት-6 ብር 15,000.00 በሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለው፣በተቀመጠው ቀነ ገደብ ሥራዎቹን ማጠናቀቅ የሚችል እና ዕቃዎቹን በራሱ ማጓጓዣ ወጪ የኦሮሚያ ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮንብረት ክፍል አቅርቦ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
 7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0118960808 ደውለው ይጠይቁን፡፡

አድራሻ፡-ፊንፊኔ (ሳር ቤት ኦሮሚያ ቢሮዎች ውስጥ)

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ