Jedda Wereda F/E/D/B

Addis Zemen Tir 15, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የተጫራቶች መመሪያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሽዋ ዞን የጅዳ ወረዳ ገ/ኢት ፅ/ቤት በስሩ ለሚገኙት መስሪያ ቤቶች ለ2013 በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉትን፡

 1. የደንብ ልብስ
 2. የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ የፅዳት እቃዎች፣ አላቂ እቃዎች
 3. የቋሚ እቃዎች የኤሌከትሮኒከስ እቃዎች ፣ የተለያዩ ሶፍት ዌሮች እና የፈርኒቸር እቃዎች
 4. የተለያዩ መጽሐፍት እና ማሽነሪዎች /ለቴከኒክ እና ሙያ ት ቤት አገልግሎት የሚውሉ
 5. የተለያዩ የመኪና እና የሞተር ሣይከል ጎማዎች፣ ከመነዳሪዎች እና የመለዋወጫ እቃዎች
 6. የግንባታ መሳሪያዎች እና
 7. የተለያዩ የስፖርት ትጥቆች እና ኳሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራቾች የሚከተለውን የጨረታ መመሪያ በጥንቃቄ ተመልከተው የመወዳደሪያ ሀሳብን እንዲያቀርቡ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ከዚህ የጨረታ መመሪያ ውጪ የሚቀርብ የመወዳደሪያ ሀሳብ ተቀባይነት እይኖረውም፡፡

ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

 1.  ማንኛውም ተጫራች ከሥራው ጋር አግባብነት ያለው የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ሆኖ የ2013 ዓም የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች የተጨማሪ የእሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ እና Tin Number ሊኖራቸው ይገባል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ ዋናውንና እና ኮፒ ለየብቻ በሰም አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 4. ለጨረታው ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ ከተራ ቁጥር 1-7/ ብር 8000.00/ስምንት ሺህ ብር/ ከጅዳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ ኮፒውን ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) በጨረታ ሰነድ እርጅናል ሰነድ ወስጥ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. ማንኛውም ተጫራች በእለፉት አመታት እና በቢሁ የሥራ ዘመን በመ/ቤታችን ተወዳድሮ በተዋዋለው ውል መሠረት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በብዛት፣ በጥራት እና በተባለው ጊዜ ውስጥ ያላቀረበ ከሆነ በዘንድሮው ውድድር ውስጥ የማይሳተፍ ይሆናል።
 6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ Yekatit 14/06/2013 ዓም በሥራ ቀናት እና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ ከተራቁጥር1- 7 የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ከጅዳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ፡፡
 7. ተጫራቾች ለውል ማስከበሪያ ካሽ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ እንዲሁም መስሪያ ቤቱ በሚያዘጋጀው ውል ላይ አምኖ መወዳደር አለበት።
 8. ተጫራቾች የሚሰጡትን ዋጋ ከነቫት (with VAT) መሆን አለበት፡፡
 9. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ Price Validity Date) ከጨረታው መከፈቻ እለት ጀምሮ Order እስኪሰጥ ድረስ ለ45 mተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆን አለበት።
 10. ተጫራቾች ለቋሚ እቃዎች ማለትም ለፈርኒቸር እና ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በሙሉ የሚያቀርቡትን የእቃ አይነት በፎቶ ወይም ሰሲዲ እንዲሁም ለደንብ ልብስ ናሙና በጨረታው መከፈቻ እለት ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ በማድረግ ያቀረበ ተጫራች ይበረታታል፡፡
 11. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች ናሙና (Sample ውል ስምምነት በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 12. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በታዘዘው ብዛት፣ ጥራት እና በተዋዋለው ጊዜ ውስጥ በራሱ ትራንስፖርት ጭኖ ጅዳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ንብረት ከፍል ገቢ ድረግ ይኖርበታል።
 13. ጨረታው በ15/06/2013 ዓም ከቀኑ 7፡45 ሰዓት ተዘግቶ በዚህ እለት ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጅዳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ቤት ይከፈታል።
 14.  በጨረታው የተሸነፉት ተወዳዳሪዎች ተሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙትን ገንዘብ በ5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡ ለአሸናፊው ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚቆየው ውል እስከ ሚፈረም ድረስ ይሆናል፡፡
 15. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀ ለውል ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
 16. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ የድርጅቱን ማህተም ፣ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን እና የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዘርፍ በትክክል ፅፈው መፈረም አለባቸው፡፡
 17. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት፡፡
 18. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • አድራሻ፡- ከሙከጡሪ ወደ ለሚ በሚወስደው መስመር ወደ ውስጥ 33 ኪሜ ገባ ብሎ ወይም ከአ/አበባ ወደ ሰንዳፋ የሚወስደው መንገድ በድሬ ማዞሪያ 37 ኪሜ ገባ ብሎ ነው ፤
 • ስልክ ቁጥር፡- 0116736269/ 0116736112

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋ ዞን

ጅዳ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት