በኢፌዲሪ መከላከያ ሚ/ር ም ሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሁርሶ

Addis Zemen Tir 13, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መያ ቁጥር ግ/ጨ/004/2013

ግዥ ፈፃሚው በአፈዲሪ መከላከያ ሚ/ር ሰላም ማስከበር ማዕከል በድሬዳዋ አካባቢ የሚገኘው የሁርሶ ኮንቲጀንት ማ/ት/ቤት በ2013 ዓ ም የ2ኛ ዙር ግዥ ለት/ቤቱ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ለመግዛት ብቁ የሆኑ ተጫራቾችን አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ዝርዝራቸው በየሎቱ የተቀመጡትን የእቃ ዓይነቶች ከታች በየሎቱ የተሰጠውን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ከታች የተገለፁትን መስፈርቶችን የምታሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

 1.  ሎት  አንድ የተለያዩ የአልባሳት የጨርቃ ጨርቅ አና ተዛማጅ እቃዎች 9,000.00
 2.  ሎት– ሁለት የተስያዩ የፅህፈት እና ተዛማጅ እቃዎች …. 15,000.00
 3.  ሎት– ሶስት የተለያዩ የፅዳት እቃዎች እና ተዛማጅ እቃዎች 8,000.00
 4.  ሎት– አራት የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እና ኤሌክትሪክ እቃዎች …. 2,000.00
 5.   ሎት– አምስት የተለያዩአላቂ የግንባታ (የኮንስትራከሽን) እቃዎች …. 2,000.00
 6.  ሎት – ስድስት የተለያዩ የቀላል ተሽከርካሪ የመኪና ጎማዎች እና መለዋወጫ እቃዎች 7,000.00
 7.  ሎት – ሰባት የተለያዩ የዕንጨትና የብረት ውጤት የሆኑ የቤትና የቢሮ እቃዎች …. 5,000 00

በመመዘኛዎች ከላይ በየሎቱ የተዘረዘሩትን እቃዎች በማቅረብ ብቃት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን መመዘኛ የሚታሟሉ ድርጅቶች በጨረታ መሳተፍና መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ማሰልጠኛ ት/ቤቱ በደስታ ይጋበዛል፡፡

 1.  ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነስርዓትና ይህንኑ አስመልከቶ የኢፊዲሪ መንግሰት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው፣፣
 2. በዘርፉ የተሰማሩበት የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ ምዝገባ ምሳከር ወረቀት ብን ነምበር፡ ቫት ተመዝጋቢ፣ የንግድ ፍቃድና የዘርፍ በግልዕ በጀርባው ዝርዝር የተገለፀ መሆን አለበት እንዲሁም ጨረታ ለመወዳደር የተሰጠ ፍቃድ ማስረጃ ኦርጅናሉና ኮፒውን ማቅረብ የሚችል ኦርጅናሉ ተመስከሮ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በተወዳደሩበት ሎት ከባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀያላቸው የታውቁ ባንኮች የሚሰጥ ስባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና በህርሶ ኮንቲጂን ማሰረጠና ት/ቤት ስም የተዘጋጀ ማስያዝ አለባቸው.
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መግዛት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበተ በ 3/5 2013 ዓ ም ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት 27/5/2013 ዓ.ም ከሰኞ እርብ በስራ ሰዓት በድሬዳዋና ዙሪያው የምገና በኩርፊ ኮንቲጂ ማተቤት በፋይናንስ ዴስከ ገንዘብ በመክፈል ከግር ዴስክ ቢሮ ቁጥር 26 ድረስ በመምጣት ሰነዱን መግዛትና መወሰድ የቻላሎ ፡ እንዲሁም በአ/ አበባና ዙሪያው የምትገኙ ጃንሜዳ በሚገኘው የሠላም ማስከበር ማዕከል ፋይናንስ ቡድን ገንዘብ በመከፈልና ሰነዱን ከየ ቡደን ቢሮ በመሄድ የጨረታ ሰነድ መግዛትና መውስድ ይችላሉ፡፡
 5. ጨረታው ፕሮፎርማ ታሽጎ ፊርማ፣ ማህተም፣ ስልክ ቁጥርና አድራሻ ተደርጎበት በኦርጅናልና በኮፒው የግዥ ፈፃሚ አድራሻ በማስቀመጥ ጠዋት 2፡00 እስከ 8፡00 ሠዓት ድረስ ለጨረታ ወደተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል . የጨረታ ሳጥኑ 8:15 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡30 ሠዓት በ27/5/2013 ዓ/ም ድሬዳዋ ነምበር ዋን መኮንኖች ከበብ ይከፈታል።
 6. . አሸናፊ ድርጅት እቃው በአንድ ግዜ በዓይነት በመጠን በጥራት ሳይጓደል ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
 7. ተጫራቶች በእያንዳንዱ ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ፊርማቸው ፣ ስማቸው፣ አድራሻቸው፣ ስልከ ቁጥራቸው፤ ዋጋ ማቅረቢያው ለስንት ቀን፣ ወር እንደሚያገለግል፣ መግለፅና ማስፈር አለባቸው፡፡
 8. ተጫራቶች እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ማህተም ፊርማ በማድረግ ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በመባል ለየብቻው በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የግዥ ፈፃሚው መ/ቤታችን የእቃ ዓይነት (ሎት) በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማሰልጠኛ ት/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
 9.  አሽናፊ ተጫራቾች የአሽናፊነት ደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ማስከበርያ 10% በሸፈነው የገንዘብ መጠን ተባዝቶ ማስያዝና የውል ስምምነት መፈፀም አለበት፡፡
 10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡ ወደፊትም በመንግስት ግዥና ጨረታ እንዳይሳተፍ ይደረጋል ያስያዙትም የጨረታ ማስከበርያ ይወረሳል፡፡
 11. የጨረታ መከፈቻ ቀን በስራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
 12. ተጫራቾች ስለማጭበርበርና ሙስና በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብሩ መሆኑን በማረጋገጥ በዚህ ቅፅ ላይ መፈረምና ማቅረብ አለባቸው፡፡
 13. በአንድ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፡፡
 14. የሚገዙትን እቃዎች መ/ቤቱን እንደአስፈላጊነቱ 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
 15. ተጫራቶች በእቃው ዓይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ ዓይነት መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡
 16. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ መ/ቤታችን ተጠያቂ አይሆንም፡፡
 17. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
 18. አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት(ወጪ) ሽፍኖ ሁርሶ ኮንቲጀንት ማ/ት/ቤት ግቢው ስቶር ድረስ የንብረት ክፍሉ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
 19. . ተጫራቾች የእቃውናሙናለሚያስፈልጋቸው ናሙና ይዞ መቅረብናሙና ማቅረብ የማይቻልባቸው ደግሞ የሚያቀርቡት እቃ ፎቶግራፍና ካታሎግ አስደግፎ ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የእቃ ስፔስፍኬሽን እና የጥራታቸው ደረጃ በግልፅ መገለፅ አለባቸው፡፡
 20. ማንኛውም ኮፒ የሚደረጉ ማስረጃዎች በትክከል መነበብና መታየት አለባቸው
 21. ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ፣ በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም፡፡ ያደረገ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡ ምንአልባት ስጠቅላላ ዋጋ ላይ ስህተት ቢፈጠር አንድ ስርዝ አድርጎ ስለ መሰረዘ ፌርማና ስም ማስቀመጥ አለበት፡፡
 22. የጨረታ ጊዜ ስኣዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ጀምሮ ለ15 ቀናት በአየር ላይ ይውላል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበትና የሚዘጋበት ሠዓት፣ ቀን፣ እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችና መመሪያዎች በሚወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ዝርዝር ይመለከቱ፡፡
 23. ተወዳዳሪዎች በጨረታ መከፈቻ ቀን (ዕለት) የጨረታ ሰነድ ሳጥን ከታሸገ (ከተዘጋ) በኋላ ዘግይተው የሚመጡ (የሚቀርቡ) መጫረቻ ሰነዶች በግዥ ህግ ተቀባይነት የላቸውም፡፡
 24. ማሰልጠኛ ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 25. . ለተጨማሪ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የማስታወቂያ ሽፋን 13/5/2013 የወጣ ዕትም ታትሞ ቀርቧል፡፡ ስለ ጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ሁርሶ ከድሬዳዋ ከተማ በ27 ኪ/ሜትር ላይ ወጣ ብሎ የሚገኝ ማሰልጠኛ ካምፕ ነው፡፡ በሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት ሁርሶ ስልክ ቁጥር 0254470115 በመደወል አስፈላጊ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በኢፌዲሪ መከላከያ ሚ/ር ም ሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት

ሁርሶ