የሸቀጥ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር 06)

ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ አምራች እና አከፋፋዮችን አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሸቀጦችን መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • የአርማታ ብረት CES 300:2013 (CES 101:2017)
  • የመደበኛ የቤት ክዳን ቆርቆሮ (CES 40:2018)
  • የቆርቆሮ ሚስማር CES:2013 (ES:95-2001)
  • ተርማል ወረቀት

ስለዚህ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. በየዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚገልፅ ደብዳቤ እና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባዋል፡፡
  2. ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ምርት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. . የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ) ለብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ Tahsas 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  5.  ጨረታው በተመሳሳይ Tahsas 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

ስልክ ቁጥር 0113690791/0113692647/011369 2439 www.eiide.com.et

በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ውጤቶች

ግዥ ዳይሬክቶሬት

Category:
Steel Raw Materials and Products, Printing and Publishing, Building and Finishing Materials, Stationery, Other Metals

Company Name:
Ethiopia’s Industrial Inputs Development Enterprise

Company Amharic:
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

Posted Date:
Hidar 30, 2013

Opening Date:
Dec 24, 2020 10:00 AM

Ending Date:
Dec 24, 2020 10:00 AM

Newspaper:
Addis Zemen

Newspaper Publish Date:
Addis Zemen Hidar 30, 2013

Publish Date:
Hidar 30, 2013

Company image
<img style="height:50px;width:50px;border-radius:50%;" src="https://tender.awashtenders.com /img/companies/palceholder.png?1556635970″/>

Address
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሐንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ|ቤት)።

Phones
[’01-13-69-20-36 ‘, ‘ 01-13-69-19-95’]

Bid document price
200 (ሁለት መቶ ብር)