Ethiopia Environment and Forest Research Center

Addis Zemen Hidar 6, 2013

ግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ያደ.ውአ..ም.ስማ 01/2013

በኢትዮጵያ የአካባቢና ደን ምርምር ኢንስቲትዩት የደን ውጤቶች ኢኖቬሽን ምርምርና ስልጠና ማዕከል

 • የጽሕፈት መሳሪያዎችን፣
 • አላቂ የቢሮ እቃዎችን፣
 • የላቦራቶሪ ኬሚካሎችንና መሳሪያዎችን፣
 • የሠራተኞች የደንብ ልብሶችን፣
 • የፅዳት እቃዎችን እንዲሁም
 • የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን መስፈርቱን በሚያሟሉ እና በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት ተጫራቾች:
 1. በጨረታው ለመካፈል በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያቁጥር (TIN) ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል::
 2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 3. . ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የላቦራቶሪ ግብአቶችና የደንብ ልብሶች የተመረቱበትን ሀገርና ዓመተ ምህረት መግልፅ ይኖርባቸዋል::
 4. ተጫራቾች በእያንዳንዱ የመወዳደሪያ እቃ የሞሉት ዋጋ ከቫት ጋር መሆን አለበት:: ከዛት ውጭ የተሞላ ነጠላ ዋጋ ሰነዱ ውድቅ ይሆናል:: ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
 5. ማዕከሉ የሚጫረቱበትን የእቃ ብዛት እንደአስፈላጊነቱ 20% በመጨመር ወይንም በመቀነስ ወይም ከውስጥ በመተው ማዘዝ ይችላል:: ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ::
 6. ማንኛውም ተጫራች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ሲያቀርቡ በሰነዱ ላይ ተፈርሞበትና የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኦርጅናልና ኮፒው ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ መስሪያ ቤቱ ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ጨታውን እስከ ሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
 7. የጨረታ ሰነዱን ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የፋይናንስና በጀት ቡድን መሪ ቢሮ በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ::
 8.  የጨረታ ማስከበሪያ ተጫራቾች ካቀረቡትከጠቅላላ የመወዳደሪያ ገንዘብ መጠን 1% በሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (unconditional bank guaranty) ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚታሰብ ከ90 ቀን ያላነሰ ማስያዝ አለባቸው። የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ የጨረታው ውጤት ታውቆ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል::
 9. ተጫራቾች የሚያቀርቡአቸውን እቃዎች ሳሪስ አደይ አበባ ንግድ ባንክ ወረድ ብሎ በሚገኘው የደን ውጤቶች ኢኖቬሽን ምርምርና ስልጠና ማዕከል ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ።
 10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል:: ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2:30 (ጠዋት) እስከ 11:30 (ከሰዓት) የመስሪያ ቤቱ መደበኛ የስራ ሰዓት ነው።
 11. የጨረታው ሳጥን 10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በቀጣዩ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ሳሪስ በሚገኘው የደን ውጤቶች ኢኖቬሽን ምርምርና ስልጠና ማዕከል ቅTir ግቢ ውስጥ በሚገኘው አዳራሽ ይከፈታል:: ነገር ግን ቀጣዩ የበዓል ቀን ከሆነ የጨረታው ሳጥን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
 12. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበውን የውድድር ጥያቄን ማዕከሉ አይቀበልም::
 13. .አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በአስር በመቶ/ በሲፒኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል:: ለውል ማስከበሪያ የተያዘው ውል መፈጸሙ እስኪረጋገጥ ድረስ ተይዞ ይቆያል::
 14. በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ያለው ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ለማዕከሉ ኃላፊ ቢሮ  ቁጥር 2 ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል::
 15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሳሪስ በሚገኘው የደን ውጤቶች ኢኖቬሽን ምርምርና የጤና ማዕከል ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0911191119፤ 0931538078, 0118898772 በመደወል ማግኘት ይቻላል::
 16. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደን ውጤቶች ኢኖቬሽን ምርምርና ስልጠና ማዕከል