• Adama

Adama Custom Commission Branch Office

Addis Zemen Hidar 22, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 4/2013

በአዳማ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት ስር ተትተው እና በኮንትሮባንድ ሲንቀሳቀሱ ተወርሰው የሚገኙ በግልፅ ጨረታ ብዛታቸው

 • 124 (መቶሃያ አራት) የሆኑ የተለያዩ ዓይነት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች፣ ኤሌክትሮኒክሶች፣
 • 108 (መቶ ስምንት) ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ75 (ሰባ አምስት) ሞተር ሳይክሎች፣ የዛገ ሚስማር(ለማቅለጫ ግብዓትነት ብቻ የሚያገለግል)፣ ኮስሞቲክስ፣ ኤሌከትሮከሶች፣ 2 ተሸከርካሪዎች፣ መነጽሮ ች እና የመኪና መለዋወጫዎችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:

 1. በአዳማ ቅ/ፅ/ቤት ለጨረታ በቀረቡት እቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው እቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በኢንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታው ደግሞ በጨረታው ዕለት ይዞ መምጣት ይኖርበታል፡፡
 2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተሰጠቀሰው ቢኖርም ግምታዊ ዋጋቸው ከ500 ሺህ ብር በታች ለሆነ እቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም፡፡
 3. በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው ቢኖርም ከአስመጪዎች ወይም ባለቤትና ቤተሰብ በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ተሸከርካሪዎቹ እና ሞተር ሳይክሎችን ላይ የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ ያለ ቅድመ ሁኔታ ጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 4. . ማንኛውም ተጫራች የግልፅና የሀራጅ ጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ መሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አ.ማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳብና ዋስትናዎ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 12 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ማግኘት ይችላሉ::
 5. በግልፅ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክሎችለእያንዳንዳቸው የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ(5%)እናበግልፅ ጨረታ ለቀረቡትኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለምድብ የሰጡትን ዋጋ 5% እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለቀረቡት ሞተር ሳይክሎች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ኮስሞቲክሶች፣ ኤሌክትሮኒክሶች የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች፣ መነጽሮች እና የዛገ ሚስማርች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን በሃራጅ ጨረታ ሰነድ ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ልክ ባንክ በተመሰከረለት (CPO) Customs Commission Adama branch office ስም ባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 6. በግልፅም ሆነ ሃራጅ ጨረታ ሽያጭ የእቃው አስመጪ ወይም ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም፡፡
 7. በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ለወጡት እቃዎች የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመሄድ ለጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO፣ የጨረታ ሰነዱ እና በተራቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱትን ሌሎች ሰነዶች ጋር በኢንቨሎፕ በማሸግ የጨረታሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን በሃራጅ ጨረታ ለሚሳተፋ ደግሞጨረታው ስሚከናወንበትእለት በሃራጅ ጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ CPO እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርብዎታል፡፡
 8. በጨረታው ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አማ ግቢ እና ቀበሌ 07 በሚገኘው በቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘኖች ስለሚገኙ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አምስተኛው ቀን ማየት ይኖርብዎታል፡፡
 9. ተጫራቾች በግልፅና ሃራጅ ጨረታ ለወጡት እቃዎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ6ኛው (ስድስተኛው) ቀን የግልፅ ጨረታው ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታው ሳጥኑ ታሽጎ 4፡15 የሚከፈት ሲሆን የሃራጅ ጨረታው ደግሞ ማስታወቂያው ከወጣ 6ኛው ቀን 5፡00 ሰዓት በአዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት በበከልቻ አዳራሽ ይጀመራል፡፡ ነገር ግን 6ተኛው ቀን ጨረታው በበዓል (እሁድ) ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይሆናል፡፡
 10. . የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡- በአዳማ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ካልቀረቡ ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
 11. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ቼክ ወይም CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡
 12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
 13. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም፡፡
 14. ከላይ በተቁ 12 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ፡ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡
 15. ከላይ የተገለፀውን የዛገ ሚስማር የሚገዛ ተጫራች ሚስማሩን ገዝቶ ከተረከበ በኋላ ለማቅለጫነት እንጂ በቀጥታ ለገበያ እንደማይሽጥ ግዴታ የሚገባ መሆን አለበት፡፡
 16. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 022-211-89-25 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ፅ/ቤት