በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴ/ሙ/ስልጠና ኤጄንሲ የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እና የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ የመስታወት በር ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር //ስልጠና ኤጄንሲ የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እና የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ የመስታወት በር ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

 1. ተጫራቾች ቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ህንፃ ላይ በሚገኘው 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 በመምጣት ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር ብቻ) ከፍለው ማስታወቂያው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
 2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ስመለኪያው መሰረት ማለትም በኪሎ ከሆነ በኪሎ በቁጥር ከሆነ በቁጥር የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር //ስልጠና ኤጀንሲ የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 6በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ በስራ ቀናት ውስጥ ተገኝተው ማስገባት አለባቸው፡፡
 3.  ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ኮሌጁ በፊደል የተጻፈውን ዋጋ በመውሰድ ጨረታውን ያወዳድራል፡፡
 4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው::
 5. ተጫራቾች ለሚገዙት ቁርጥራጭ ብረታ ብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ወስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ...ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
 6. ጨረታ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 800 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ 4 ፎቅ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
 7. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው 7 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ ክፍያ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮሌጁ ገቢ ይደረጋል፡፡
 8. አሸናፊ ተጫራቹ በራሱ ወጪ በመንግስት በምድር ሚዛን ብረታብረቶችን ያስመዝናል፡፡
 9. ኣሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪዎችንና ንብረቶችን ከፍያውን ከፈፀሙ በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው::
 10. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
 11. የጨረታ ሰነድ ከተከፈተ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ስጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የለውም፡፡
 12. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከጨረታው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም፡፡
 13. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
 14. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0118932675 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 15. ኮሌጃችን የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡ መሪ 40/60 ኮንዶሚያም ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር 0118932675

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር //ስልጠና ኤጄንሲ

የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ