North Shewa Zone Antso G/w/ Finance and Economic Development Bureau

Addis Zemen Yekatit 2, 2013

የመስኖ ቦይ ግንባታ ለማሠራት የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአንፆ/ገ/ወ/ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ለአንፆ/ገ/ወ/ግብርና ፅ/ቤት በAGP ፕሮጀክት አሰለሌ ቀለበት ወንበር ቀበሌ ልዩ ቦታው የአምቦ ውሃ ጎጥ የመስኖ ቦይ ግንባታ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ መ/ቤታችን ግዥውን የሚፈፅመው በጥራትም ሆነ በዋጋ ብቆ መሆናቸውን አረጋግጦ የመረጣቸውን የውሃ የግንባታ ተቋራ ድርጅቶችን ብቻ ሲሆን፤ ይህ ግዥ ተግባራዊ የሚሆነው በገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በአገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላላቸው ግዥዎች አፈጻፀም ባወጣው መደበኛ የጨረታ ሠነድ ውሰጥ በተጠቀሱት አጠቃላይ የውል ሁኔታዎች መሠረት ይሆናል፡፡ አጠቃላይ የውል ሁኔታዎቹ በዚህ የመወዳደሪያ ሐሳብ መጠየቂያ ሠነድ ውስጥ ከሌሉና ማየት ከፈለጉ መ/ቤታችንን ጠይቀው ማግኘት ይቻላል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሣተፍ የምትፈልጉ፡

 1. የማወዳደሪያ ሐሳቦቹ በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ ውስጥ ሆኖ ከ2/6/2013 ዓ.ም እስከ 1/7/2013 ዓ.ም ድረስ ለአንፆ/ገ/ወ/ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ግዥ ን/ቡ/ ሥራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 6 ከቀኑ 4፡00 ድረስ መቅረብ አለበት፡፡
 2. ጨረታውን መወዳደር የምትፈልጉ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከ2/6/2013 እስከ 1/7/2013 ድረስ ግ/ፋይ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር G-01 ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመምጣት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይቻላል፡፡
 3. ጨረታው በ2/7/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡01 ሰዓት የሚታሸግ ሲሆን፤ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በአንፆ/ገ/ወ/ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ግዥ ን/ቡ/ ሥራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል።
 4. ጠቅላላ የግንባታ ሥራ ዋጋው በቁጥርና በፊደል መገለጽ አለባቸው፡፡ በቁጥርና በፊደል በተገለፀው የዋጋ መጠን መካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለፀው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪ በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ በነጠላ ዋጋ የተገለፀው ተቀባይነት አለው፡፡
 5. ተጫራቾች ያቀረቡት የመወዳደሪያ ሐሳብ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ፀንቶ የሚቆይ፣ የማይቀየር፣የማይካስና ማስተካከያ የማይደረግለት መሆኑን መረጋገጥ አለባቸው፡፡
 6. የቀረበው ግንባታ ሥራ ጨረታ ዋጋ በውል ላይ በተቀመጠው ቀን መሠረት ፀንቶ ይቆያል፡፡
 7. አሸናፊ ተጫራቾች የግንባታ ሥራን ሙሉ በሙሉ በውለታው መሠረት ማጠናቀቃቸው ከተረጋገጠ በኋላ ቢበዛ በሰባት ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያ ይከፈላቸዋል፡፡ ለግንባታ ሥራ እንደአስፈላጊነቱ እየታየ ለተሰራው ሥራ ብቻ ክፍያ መፈፀም የሚቻልበት ሁኔታ ሊታይ ይችላል፡፡
 8. የመወዳደሪያ ሐሳብ ማቅረቢያ ቋንቋ በአማርኛ ነው፡፡
 9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ታክስን የማያካትትና የሚያካትት መሆኑ በትክክል መግለጽ አለበት፡፡ ካልተገለፀ ግን ታክስን እንዳካተተ ይቆጠራል፡፡
 10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የማወዳደሪያ ሐሳብና ዋጋ ላይ ፊርማቸውንናቀንና የድርጅቱን ማህተም ማሣረፍ ይገባቸዋል።
 11. ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያውን በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተማራቶቹ ምርጫ የጠቅላላ ዋጋውን 220,000/ ሁለት መቶ ሃያ ሺህ ብር /በጥሬ ገንዘብ /CPO/ በፖስታ ውስጥ ለብቻው አሽጎ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 12. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ግንባታ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ከታወቁ ባንኮች የተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
 13. የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች አሸናፊ ውል ከፈፀመ በኋላ የሚመለስ ሲሆን፤ ለአሸናፊው ድርጅት ውል ፈጽሞ 10% የውል ማስከበሪያ እንዳስያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ይመለስለታል፡፡
 14. ተጫራቾች ሕጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር ያላቸው /የቲን ተመዝጋቢነት፣ የቫት ተመዝጋቢነት እና የታደሠ የብቃት ማጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡፡
 15. ተጫራቾች በዘርፉ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው እና ደረጃ 5 እና በላይ መሆን አለባቸው፡፡
 16. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 17. መ/ቤቱ የሚያሰራውን ሥራ 20 ፐርሰንት ሃያ ፐርሰንት/ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት አለው።
 18. ማንኛውም ተጫራች የሚሠራበትን ቦታ በሣይት/ማየት ይኖርበታል፡፡

ማሣሰቢያ፡- ተጫራች የመወዳደሪያ ሐሳባቸውን የሚጠበቅባቸውን መረጃ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ በሰሜን ሸዋ

ዞን በአንፃ/ወ/ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ግዥ ን/አስ/ቡድን