East Gojam Zone Administration Finance and Economic Development Bureau

Addis Zemen Tahsas 26, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ገ/ኢ/ል/ትብብር/ቢሮ የምስራቅ/ጎ/ዞ/ገ/ኢ/ት/መምሪያ የግዥና ን/አስ/ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል፡

 • ሎት 1.ደንብ ልብስ:- ብትን ጨርቅ፣
 • ሎት 2 ቆዳ ጫማ፣
 • ሎት 3.የጽሕፈት መሳሪያ፣
 • ሎት 4. የኮምፒዩተርና ተዛማጅ እቃዎች፣
 • ሎት 5 ኤሌክትሪክ እቃዎች፣
 • ሎት 6.ድምፅና ምስል እቃዎች፣
 • ሎት 7.የአፈር ምርምር ኬሚካል እና የእፅዋት ዘር ላቦራቶሪ እቃ፣
 • ሎት 8. የውጭ ፈርኒቸር እቃዎች፣
 • ሎት 9. ሕንፃ መሳሪያ፣
 • ሎት 10. የህትመት፣
 • ሎት 11. የስፖርት ትጥቅ፣
 • ሎት 12 ጀነሬተር፣
 • ሎት 13 የፅዳት እቃዎች፣
 • ሎት14የማሽነሪ መለዋወጫ እቃ፣
 • ሎት 15.የባዮ ጋዝ ስቶቭና ዶም ፓይፕ እቃዎች፣
 • ሎት 16. ለባዮ ጋዝ ግንባታና የጋዝ መስመር ዝርጋታ የሚያገለግሉ ፒፒአር ቱቦ መገጣጠሚያ፣
 • ሎት  17. የባዮ ጋዝ ቁሳቁሶች፣
 •  ሎት 18 የመኪና ጎማና ካለመንዳሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ

በዚህም:

 1. በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
 3. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
 5. በተጫራቾች የሚቀርበው የመወዳደሪያ ዋጋ ለ40 ቀን ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።
 6. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይችላሉ።
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲ.ፒ.ኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመስሪያ ቤቱ በመሂ1 ማስያዝ አለባቸው።
 9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በገ/ኢ/ት/መምሪያ በግዥ/ን/አስ/ቡድን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛትና የመወዳደሪያ ሃሳብ ሞልቶ እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ሆኖም የጨረታው መክፈቻ ቀን የበዓላት ቀን ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
 10. የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም ከሆነም ፈርማ መደረግ አለበት / ኮሬክሽን ፍሉድ መጠቀም አይቻልም።
 11. ተጫራቾች መ/ቤቱ ካዘጋጀው የሥራ ዝርዝር /ስፔስፍኬሽን/ ውጪ መጨመርም ሆነ መቀነስ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
 12. በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
 13. በሎት 16 የተጠቀሰው የባዮ ጋዝ ስቶቭና ዶም ፓይፕ እቃዎች ሎት ግዥ ለባለሙያ ክትትል እንዲመች ደብረማርቆስ ከተማ ላይ አምርቶ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ እና በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው ::
 14. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ወይም ውል የያዙባቸውን እቃዎች በምስ/ጎ/ዞ/መምሪያዎች ባሉ የፑል ንብረት ክፍሎች ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 15. በሎት 1፤2፤7፤11 እና 14 የተጠቀሱ ሎቶች በድጋሚ ጨረታ የወጡ መሆኑን እንገልፃለን።
 16. በሎት ተራ ቁጥር 2 ላይ ውድድሩ በተናጠል ዋጋ የሚታይ ሲሆን ሌሎች ሎቶች ግን በጥቅል ወይም በሎት ድምር ውጤት ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ አሸናፊ ይሆናል ፤ የሁሉም ዋጋ መሞላት አለበት ሁሉንም የጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ አለመሙላት ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
 17.  የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
 18. ደንብ ልብስ ሰር 1.ብትን ጨርቅ ሎት ፤ 2ቆዳ ጫማ ሎት ፤ 11. የስፖርት ትጥቅ ሎት እና.16.ለባዮ ጋዝ ግንባታና የጋዝ መስመር ዝርጋታ የሚያገለግሉ ፒፒአር ቱቦ መገጣጠሚያ ሎት፤7.የአፈር ምርምር ኬሚካል እና የእፅዋት ዘር ላቦራቶሪ እቃ ሎት በተመለከተ መ/ቤቱ ባቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
 19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 20. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡-0587716817/0587713158 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአብክመ ገ/ኢ/ል/ትብብር/ቢሮ

የምሥራቅ/ጎ/ዞ/ገ/ኢ/ት/መምሪያ የግዥና ን/አስ/ቡድን