• Arsi

Arsi University

Addis Zemen Tir 8, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር በአርሲ ዩ.በቆ.ካ. 01/2013

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሣይንሶችና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ (በቆጂ ካምፓስ) ለ2013 ዓም በጀት ዓመት ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፤

መለያ

የጨረታው ዓይነት

የጨረታው ማስከበሪያ ብር

ደረጃ

ሎት1

የከብቶች መኖ

50,000

 

ሎት2

የማገዶ እንጨት

30,000

 

ስለዚህ በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፤

  1. የዘመኑ የታደሠ የንግድ ፍቃድ።
  2. ከመንግሥት ግዥና ን/አስተዳደር ኤጀንሲ የንግድ ሥራ ምሥክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  3. የተዕ.ታክስ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው፡፡
  4. በጨረታው ለመሣተፍ የሚያስችል የድጋፍ ማሥረጃ ከግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ በአቅራቢነት የተመዘገቡ፡፡ በዚሁ መሠረት ተጫራቾች የጨረታው ሠነድ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሣይንሶችና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ (በቆጂ ካምፓስ) ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሠነድ ቴክኒካል ኦርጅናል ለብቻ በአንድ ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጅናል ለብቻ በአንድ ፖስታ ሆኖ ቴክኒካል ኮፒ እና ፋይናንሻል ኮፒ ደግሞ በአንድ ፖስታ /ኤንቬሎፕ/ ሲፒኦ (CPO) ለብቻ በአንድ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ለተዘጋጀው በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ጨረታ ሣጥን ውስጥ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታው ሣጥን በጨረታው የመጨረሻ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሽጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሣይንሶችና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ (በቆጂ ካምፓስ) ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ውስጥ ይሆናል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  8. ጨረታውን አሸንፎ በወቅቱ ውል ለማያሥር የጨረታው አሸናፊ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ (CPO) አይመለስለትም፡፡
  9. ዩኒቨርሲቲው (ኮሌጁ) የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0223321208 /0223320929 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በአርሲ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ሣይንሶችና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ (በቀጂ ካምፓስ)

በቆጂ