Amhara Water Works Construction Enterprise

Addis Zemen Hidar 11, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር

AWWCE NCB main 03/2013

በአማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

 • የፅህፈት መሳሪያ፣
 • የፅዳት እቃዎች እና
 • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
 1.  ተወዳዳሪዎች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፡ የምዝገባ የምስከር ወረቀት፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና የገጽ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
 2. ተጫራቾች የተጠየቁትን የፅህፈት መሳሪያ፣ የፅዳት እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የሚያቀርቡበትን ዋጋ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው:: ስርዝ ድልዝ በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ከተደረገ አጭር ፊርማ ማድረግ አለበት። ካልተደረገ ግን ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
 3. የሚቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ሕጋዊ የድርጅቱ ተወካይ ስም፣ ፊርማና ማህተም ይኖርባቸዋል።
 4. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ የእቃዎችን እና የመጫኛን ዋጋየሚሸፍን ይሆናል። ሌሎች ከእቃዎች ጋር የተያያዙ ማንኛውም ወጪዎች በተሰጠው ዋጋ ላይ ተጠቃለው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
 5. በዚህ ግልፅ ጨረታ የሚሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ ቢያንስ የዋጋ ማቅረቢያው ለድርጅታችን ከደረሰበት ቀን ጀምሮ ለአንድ ወር ተኩል /ለ45 ቀናት/ የፀና ይሆናል።
 6. ተጫራቾች እቃዎቹን የሚያቀርቡበትን ጊዜ ውል ከተያዘ ጀምሮ /Delivery Time/ በ45 አርባ አምስት/ ቀን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
 7. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ20 ቀን በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፤30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
 8. ተጫራቹ አሸናፊ ሆኖ ከተመረጠ ያለምንም ቅድመ ክፍያ በራሱ ወጭ እቃዎችን ያቀርባል።
 9. እቃዎችን በሚፈጽመው ውል መሠረት ያላቀረበ አሸናፊ አቅራቢ ለዘገየበት እቃዎችን ጠቅላላ ዋጋ 0.1% በየቀኑ መቀጫይከፍላል። ሆኖም ይህ መቀጫ ከጠቅላላ ዋጋው 10% ሊበልጥ አይችልም። ነገር ግን የቅጣት ጠቅላላ ዋጋው ከ10% ከበለጠ ገዥ ለሻጭ ማሳወቅ ሳይገደድ ውሉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።
 10. ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮች ሊከሰቱ በሁለቱ ወገን በሻጭ እና በገዥ/ የጋራ ውይይት ችግሩ ይፈታል። በጋራችግሮችን ለመፍታት ካልተቻለ በሚመለከተው ፍርድ ቤት ሁለቱም ወገን ቀርበው በሚወሰነው ውሳኔ የሚፈጠረው አለመግባባት ይፈታል።
 11. እቃዎችን መጫኛ ማውረጃ ተጫራቹ በራሱ ውጭ ይሸፍናል።
 12. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ዋስትና ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ/ ሲፒኦ ወይም እንኮንድሽናል ቢድ ቦንድ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
 13. የጨረታ ማስከበሪያ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይደረጋሉ። ተጫራቹ ኣሸናፊ ሆኖ ከተመረጠ ያለምንም ቅድመ ክፍያ በራሱ ወጭ እቃዎችን ያቀርባል።
 14. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
 15. ጨረታው ሲከፈት የጨረታውን ሂደት ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ። ለወደፊቱም ድርጅቱ በሚያደርገው ሌሎች ጨረታዎች ላይ አይሳተፉም። ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ይወረሳል።
 16. ድርጅቱ አሸናፊውን ተጫራቶች በሚመረጥበት ጊዜ የሚገዛውን እቃ ብዛት /መጠን/ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 30% ፐርሰንት ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል
 17. . አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት። ያላስያዘ እንደሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው። የደረሰው ጉዳት ከውል ማስከበሪያው ሰላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከኣቅራቢው መጠየቅ ይችላል።
 18. ጨረታውን ለማሸነፍ እንዲረዱት ለማንኛውም የድርጅቱ ሃላፊ ወይም ሠራተኞች መደለያ የሰጠ ተጫራች አግባብ ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ድንጋጌ መሠረት መጠየቁ እንደተጠበቀ ሆኖ ከጨረታው እንደሚሰረዝ፣ አሸንፎ ውል ሲዋዋልም ውሉ ይሰረዛል::
 19. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ በመግዛት የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋናው ቢሮ አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው ህንፃ ቢሮ ቁጥር 32 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
 20. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 • ማሳሰቢያ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ስልክ ቁጥር 058-222-1479 ወይም058-226-5203 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
 • ፋክስ ቁጥር 058-222- 1335
 • የአማራ ውሃ ሥራዎችኮንስትራክሽን ድርጅት ባህር ዳር