Weldiya City Finance Economic Development Bauero

Be'kur Hidar 14, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልል በሰ/ወሎ/ ዞን የወልዲያ ከተማ አስ/ር/ኢ/ል/ከ/አገ/ፅ/ቤት በ2013 በጀት አመት በአለም ባንክና በመደበኛ በጀት ለሚያሰራው የመሰረተ ልማት ስራዎችና የእቃ ግዥና የማሽነሪ ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡

ለዚህ ጨረታው ለመንገድ ጥገና ስራ መሳተፍ ለምትፈልጉ ሁሉ በደረጃ 6 እና በላይ ሙያ ባላቸው RC እና GC የስራ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡

 • ሎት 1 3 ሳይት መንገድ ጥገና ስራ በመደበኛ በጀት
 • ሎት 2 2 ሳይት መንገድ ጥገና ስራ በመደበኛ በጀት
 • የመንገድ ከፈታ ስራ በመደበኛ በጀት የማሽነሪ ኪራይ ሎት1
 • የኮብል ስቶን የመሬት ቆረጣ ስራ በመደበኛ በጀት የማሽነሪ ኪራይ ሎት2
 • ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በአለም ባንክ በጀት
 • ሎት 2 የጋቢዮን ሽቦ ግዥ በአለም ባንክ በጀት

ተቋራጮችና አቅራቢዎች አስፈላጊ የሆኑትን የግንባታ ማቴሪያሎትና የእጅ ዋጋ ችለው ለሚሰሩ ተወዳዳሪዎችና የእቃ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮችና አቅራቢዎች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ ስለዚህ፡-

 1.  የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
 2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ አለበት፡፡
 3.  ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
 4.  ማንኛውም የስራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5.  ከአማራ ክልል ውጭ የሚመጡ ተጫራቾች በሚንስተር መ/ቤቱ የኮንስትራክሸንና ኢንዱስትሪ ልማት ቁጥጥር ባለስልጣን የምዝገባ ሰርትፈኬት ወይም አጭር ምዝገባ ማቅረብ አለበት፡፡
 6.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ/ ገቢ ሆኖ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርበታል
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ወ//ከ/አስ/ር/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመምጣት ለእያንደንዳቸዉ ሰነዶች የማይመለስ 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
 8. በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ለተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማሰያዝ አለብዎት፡፡
 9.  በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤና የመልካም ስራ አፈጻጸም ወቅታዊ የሆነ መረጃ በሃላፊ የተፈረመ ማቅረብ አለበዎት፡፡
 10.  በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ እና 10 በመቶ አስይዘው ወደ ስራ መግባተዎ ሲረጋገጥ እንደ የፕሮጀክቱ ዓይነት እስከ 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ይሰጣል፡፡
 11. ማንኛውም የግዥ ወይም የግንባታ ስራዎች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ መሙያ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ እንዲሁም የማይነበብ ወይም ተደጋግሞ የተጻፈ ያቀረቡ ተወዳዳሪዎች /ተጫራቾች/ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
 12. የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናልና በኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ሳይት እና እቃ ዓይነት በፖስታው ላይ በመጻፍና በማዘጋጀት የድርጅቱን ማህተምና ፈርማ ሙሉ አድራሻ በመግለጽ በተለያየ ፓሰታ አሽጎ በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ማሰገባት ይኖረባቸዋል፡፡
 13. ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 12 የተዘረዘሩት መስፈርቶች ለሁሉም ተጫራቾች (ተወዳዳሪዎች) ገዥ ይሆናል፡፡

1. ሎት 1 እና ሎት 2 የመንገድ ጥገና ስራ በወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮን አገልግሎት ፅ/ቤት በ2013 ዓ.ም በመደበኛ በጀት በጀት ለሚያሰራው የመንገድ ጥገና ስራ ሎት 1 ሦስት ሳይት የመንገድ ጥገና ስራ ኮድ woldia – CW- GRm- CIP –02—01–2020/21 እና ሎት 2 ሁለት ሳይት የመንገድ ጥገና ስራ ኮድ woldia – CW- GRm- CIP–02—02–2020/21 ያሉትን የመንገድ ጥገና ስራ በደረጃ 6ና በላይ ሙያ ባላቸው RC እና GC የስራ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ለመንገድ ጥገና ስራ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የማሽነሪና ማቴሪያሎች፤ የእጅ ዋጋ ችሎ ወይም አቅርቦ በደረጃ 6 በላይ ሞያ ባላቸዉ RC እና GC የስራ ተቋራጮች መስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በተዘጋጀው ፕላንና የሰራ ዝርዝር መሰረት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 14/03/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 05/04/2013 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሰራ ሰአት የጨረታ ሰነዱን በወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገልግሎት ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጧዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማሰገባት አለበዎት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 05/04/2013 ዓ.ም ከጧዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

2. የማሽነሪ ኪራይ ተጫራቾች

በወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮን አገልግሎት ፅ/ቤት በ2013 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለሚያሰራዉ የተለያዩ ሳይቶች አድስ የመንገድ ከፈታ ስራ የማሽነሪዎች ኪራይ ሎት1 የትራንስፖርት፤ሎቤድ፤ነዳጅ፤ጥበቃና ማንኛዉንም ማቴሪያል ችሎ ኮድ woldia – CW- GR- CIP-01—01–2020/21 እና በ2013 ዓ.ም በመደበኛ በጀት ለሚያሰራዉ የኮብል ስቶን የመሬት ቆረጣ ስራ የማሽነሪ ኪራይ ሎት 2 የትራንስፖርት፣የሎቤድ፤ነዳጅ፤ጥበቃና ማንኛዉንም ማቴሪያል ችሎ ኮድ woldia – CW- GR- CIP-01—02–2020/21 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 14/03/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 29/03/2013 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮን/ አገልግሎት ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ፖስታውን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለበዎት የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 29/03/2013 ዓ.ም ከጧዋቱ 3፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከጧዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

3. ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ ሎት 2 የጋቢዮን ሽቦ

በወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮን አገልግሎት ፅ/ቤት በአለም ባንክ በጀት በ2013 ዓ/ም የኤሌክትሮኒክ እቃዎች ሎት 1 እና የተለያዩ መጠን ያላቸው ጋቢዮን ሽቦ ከነማሰሪያዉ ሎት 2 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን አሟልተው መወዳደር ለምትፈልጉ ሁሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 14/03/2013 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 29/03/2013 ዓ/ም ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በወ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮን/ አገልግሎት ፅ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ፖስታውን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከስአት 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለበዎት የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 29/03/2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከስአት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡ በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን ንብረት በራስዎ ወጭ አጓጉዘው ወ/ከ/አገ/ንብረት ክፍል ገቢ ያደረጋሉ፣ ካሸነፉት ንብረት ውስጥ ትክክለኛውን እቃ ካላቀረቡ በራስዎ ወጭ መልሰው ትክክለኛውን እቃ ያቀርባሉ፡፡ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ሁሉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 03 33 31 03 22 እና 03 33 31 18 61 ወይም 03 33 31 13 31 በመደወል መረጃ ማገኘት ይቻላል፡፡ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- የመንገድ ጥገና ስራ አሸናፊ ከሆኑ ቴስት ሪዛልት ያቀረባሉ፤፤

የወልዲያ ከተማ አስ/ር/ኢ/ል/ከ/አገ/ፅ/ቤት