Mida Wereda Berima Health Post

Addis Zemen Hidar 10, 2013

ልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብ/ክ/መ በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ በሬማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን

 • የደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፤ የተዘጋጁ የደንብ ልብስ ጫማዎችና ሸሚዞች ፣
 • አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች ፤
 • ሌሎች አላቂ የቢሮ እቃዎችንና
 • የፅዳት እቃዎች ፣
 • ቋሚ የቢሮ እቃዎች፤
 • የቢሮ ፈርኒቸር ፤
 • የልብስ ስፌት እና ህትመት፤
 • ኤሌክትሮኒክስ ፤
 • መስተንግዶ
 • የመኪና መለዋወጫ እቃ እና ጎማ፣ የቢሮ ጥገና በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጫረታው እንድሳተፉ ይጋብዛል።
 1.  በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ በዘመኑ ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን እንዲሁም በጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ድምር ከብር 50,000.00 ( ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
 2. የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰአት በተከታታይ እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰአት ድረስ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) ብቻ በመከፈል ከሬማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 መውሰድ ይችላሉ።
 3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ተሞልቶ ለጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና 1 ፐርሰንት ቢድ ቦንድ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
 4. ተጫራቾች በአዲስ የንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ መደቦችና የተሰማሩበትን የስራ መስኮች በተገለጸው ትንታኔ ካልሆነ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ።
 5. ተጫራቾች የእቃውን የዋጋ ዝርዝርና በጨረታ መወዳደሪያ ላይ ስም ፊርማናማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀንጀምሮ 15ኛው ቀን 3፡30 (ሶስት ተኩል) ድረስ በሬማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል
 6. ጨረታው ተጫራቾች በአካል ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይምባልተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 በሬማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ጊቢ ውስጥ ይከፈታል።
 7.  የጨረታው አሽናፊ ተጫራቾች እቃውን በሬማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ አለበት።
 8. ተጫራቾች በተቀመጠላቸው ክፍት ቦታ ላይ የእቃውን ሞዴል ብራንድ ኔም ወይም መለያ የተመረተበት አገር አካቶ ካሪሞሉ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ።
 9. ተጫራቾች የደንብ ልብሶችን የፕሪተር ቀለም የፋክስ ቀለም ናሙና ካላቀረቡ ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ።
 10. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ጥራት ያለው ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 11. በዚህ ጨረታ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ በግዥ ዙሪያ የውይይት መድረክ ስላዘጋጀን ጨረታው በወጣ በ8ኛው ቀን በመ/ቤቱ ተገኝተው በውይይቱ እንዲሳተፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
 12. . መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊልየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 መረጃ በስልክ ቁጥር 0926763684 ወይም 0920056828 ደውለው ይጠይቁን ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በሚዳ ወረሞ ወረዳ የሬማ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ