Angolela and Tera Woreda F/E/D/Bureau

Addis Zemen Jan31,2021

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03/2013

ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የእንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ዋና ፅ/ቤት በመደበኛ በጀት

 • ሎት 1 አነስተኛ ቋሚ እቃዎች
 • ሎት 2 የተዘጋጀ መጋረጃ
 • ሎት 3 ፕላስቲክ ምንጣፍ
 • ሎት 4 የመኪና ጎማ
 • ሎት 5 የስፖርት ትጥቅ
 • ሎት6 የመኪና መለዋወጫዎች የመሳሰሉትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስስሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ፡

 1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN No/ ያላቸውና ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ እና ለመመዝገባቸው የምስከር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ።
 2. እቃዎቹን በአንድ ጊዜ በአይነት በመጠን በጥራት ሳያጓደል ማቅረብ የሚችል።
 3. ተጫራቾች የጨረታ ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ (ወይም ማሻሻያ ማድረግ ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውን አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትየጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍከሬዲት ወይም ገ/ኢ/ት/ዋና ፅ/ቤት በመሂ፡ ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ መያያዝ አለበት። የእቃ ግዥ መ/ቤቱን የተጫራቾችን ስምና አድራሻ እንዲሁም የግዥውን የእቃ አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 5.  ጨረታው በዚሁ እለት በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከጠዋቱ4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም።
 6.  16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል፤
 7. መ/ቤቱ ጨረታውን በተናጠል አልያም በጥቅል ሊያወዳድር ይችላል።
 8. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 10.000 /አስር ሺህ/እና ለአገልግሎት ከብር 3000/ሶስት ሺህ/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ከፍያ ላይ 2% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል።
 9. . ተጫራቾች በእቃ አይነትም ሆነ መጠን በጨረታው በሙሉ ወይንም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ ሆኖም አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችሉም።
 10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት።
 11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት አን/ጠ/ ወ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ጫጫ ከተማ ድረስ በየንብረት ከፍሉ ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል።
 12. ተጫራቾች ከአንድ ጨረታ በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የሚያሲዘት የጨረታ ማስከበሪያ በተናጠል ወይንም በየሎቱ ለየብቻው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
 13. . ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ በሚሆኑበት ጊዜ የእቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ውል ከመግባቱ በፊት ጥራት ያለው ናሙና ይዞ መቅረብ አለበት።
 14. . የጨረታ ሰነዱን በአን/ጠ/ወ/ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰአት ለእያንዳነዱ ሰነድ የማይመለስ 50 ብር መግዛት ይችላሉ።
 15.  በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል።
 16. መ/ቤቱ የሚፈጽመው የግዥ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20 ፐርሰንት መጨመር እና መቀነስ ይችላል።
 17. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 18. . ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከእ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪሜ ርቀት ስደሴ መስመር ላይ ነው።
 19. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-6 32-0147 ወይም 011 6-32-07 45 /011-6 32-03-04 ደውለው ይጠይቁ።

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን በአንጉስሳ ጠራ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ

ትብብር ዋና ፅ/ቤት የግዥና ንብረት

አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት