• Amhara, Wollo
 • Applications have closed

ANRS Kalu Woreda Finance and Economic Development Bureau

Addis Zemen Tahsas 25, 2013

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን የቃሉ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤትየግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቃሉ ወረዳ የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀከት አገልግሎት የሚውሉ በግዥው መለያ ቁጥር ቃሉ 01/013: ቃሉ 04/0/13 እና ቃሉ 05/013 የተዘረዘሩትን

 • ሎት 01 ፣ የግንባታ እቃ ግዥ፣ 
 • ሎት 04 የእንስሳት መኖ መመገቢያና ውሃ መጠጫ እና የእንስሳት ምርት መሰብሰቢያ እቃ ግዥ እና 
 • ሎት 05 : የውሃ ማጠራቀሚያ በርሚልና ውሃ መቅጃ ጀሪካን ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ

የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

 • 1. ተጫራቾች ህጋዊ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቲን ነምበር ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና መረጃ ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለባቸው፡፡
 • 2. በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
 • 3. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ የሚያቀርቡት ዋጋ ከነቫቱ ነው፡፡
 • 4 የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 • 3 ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከፋይናንሻል ፕሮፖዛል ከኦሪጅናል ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • 6. የሚፈለገውን የእቃ አይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 • 7.ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ25/04 /2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 25/5/2013 ዓም በ 11፡30 ሰዓት ድረስ ቃሉ ወረዳ ገ/ኢ/ት ቢሮ ቁ 9 በመምጣት የተዘጋጀውን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
 • 8ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለሎት 01(የግንባታ እቃ ግዥ) 73,000 /ሰባ ሦስት ሺ /ለሎት፡ 04 ( የእንስሳት መኖ መመገቢያና ውሃ መጠጫ እና የእንስሳት ምርት መሰብሰቢያ እቃ ግዥ 14,500 /አስራ አራት ሺ አምስት መቶ ብር/ እና ለሎት 05 (የውሃ ማጠራቀሚያ በርሜልና ውሃ መቅጃ ጀሪካን ግዥ 8,000 /ስምንት ሺብር /ማስያዝ አለባቸው፡፡ የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ በቢድ ቦንድ ከሆነ ከ120 ቀን ያነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም፡፡
 • 9የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የዋጋውን የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
 • 10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን የቴክኒክ ዶክመንትና የዋጋ ማቅረቢያ (ፋይናንሻል ዶክመንት) ዋናና ቅጅ በማለት ለየብቻ በፖስታ አሽጎ ስምና አድራሻውን በመጻፍ ቃሉ ወረዳ ገ/ኢት ፅ/ቤት ግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 24/05/2013 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት በማስገባት በ25/05/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚህ ዕለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የሌለው ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በመከፈቻው ዕለት የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም 
 • 11 የጨረታ መከፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 • 12.አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፈበት ዋጋ በአቃቤ ህግ ፅ/ቤት ቀርቦ ውል ለመውሰድ ፍቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡
 • 13 ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር የሚገባው ሲሆን ስርዝ ድልዝ ሲያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
 • 14 መ/ቤቱ ከአሸናፊው ድርጅት (ግለሰብ) ከአሸነፈው እቃ ወይም ገንዘብ መጠን ላይ 30% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • 15 በተጨማሪም ተጫራቹ ፕሮጀከቱ ከሀገራችን መንግሥት ጋር ለተዋዋለባቸው የግዥ አፈጻጸም መመሪያዎች ተገዥ መሆን አለበት፡፡
 • 16. አሸናፊው ድርጅት ቃሉ ወረዳ ንብረት ክፍል ድረስ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ መሆን አለበት፡፡
 • 17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • 18. ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር ነው:: አንድ ተጫራች በአንዱ ወይም በሁሉም ሎት መወዳደር ይችላል፡፡
 • 19 አሸናፊው ተወዳዳሪ ኦርጅናል እቃዎችን ማቅረብ እንደተጠበቀ ሆኖ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ውል ከመወሰዱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም ጨረታውን ማሸነፉ ከተነገረ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
 • 20. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ ቃሉ ወረዳ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡ 0335514657 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአብክመ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ

 ቃሉ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት

የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን

ኮምቦልቻ