Shebe Berenta Finance and Economy Bureau

Addis Zemen Tir 7, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 03/2013

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥ/ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት የግዥ ቡድን በወረዳ ለሚገኙት ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል 

 • ሎት1፦ የሲሚንቶ፣ ቆርቆሮ እና ሚስማር፣ 
 • ሎት 2፡- ኤሌክትሮኒክስ ጨረታ፣ 
 • ለሎት 3፡- የመኪና ጎማ አወዳድሮ ለመግዛት/ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

 1. የተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ 1 ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብርየከፈሉበትን የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ፣ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የቲን ነምበር /የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ የሆኑ የቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 3.  ሁሉም የእቃ አቅርቦት ተወዳዳሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን በመያዝ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የእቃ አቅርቦት ስራውን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦት መስራት /ማቅረብ/ የሚችል፡፡
 4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች በጥንቃቄ አሽገውና ማህተም አድርገው ማቅረብ አለባቸው:: የሚፈለገው ፖስታ በሁለት ቅጅ ከሆነ በፖስታው ላይዋናውንና በጽሁፍ ዋናና ቅጅ በማለት ለይተው ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በሚሞሉት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለበት ፓራፍ ማድረግ አለባቸው፡፡
 5. እያንዳንዱ ተጫራች ሰነዱን የሚያሟሉት በነጻ ገበያ ዋጋ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡ ለሞሎትም ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1: 14,000.00 /አስራ አራት ሺህ ብር ለሎት2, – 20,000.00/ሃያ ሺ ብር ብቻ/ ለሎት 3፡- 6,000.00 /አስራ ስድስት ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና ስሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከማጠቃለያ ፖስታው ጋር ለብቻው በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 6. ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው ስራ የጹሁፍ ማመልከቻ በማቅረብ ሎት 1-3 100.00 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ብር በመከፈል ከቢሮ ቁጥር 06 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
 7. ይህ ማስታወቂያ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 4፡00 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓል ቀን/ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት የማያስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 8. አቅርቦቱን ለማቅረብ /ለመስራት ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ በገቡት ውል መሰረት ማጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡ ሆኖም ከአሸነፉበት ዋጋ የዋጋ ልዩነት ሲኖር ምንም አይነት ጭማሪ የማናደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
 9.  በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
 10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅታቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።
 11.  የተጫራቾች የመጫረቻ ድጋፍ ሰነዶቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን አለበት፡፡
 12. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ለውል ማስከበሪያ የሚሆን 10% ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ እና ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
 13. ማሳሰቢያ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ለእቃ አቅርቦት፤/ለአገልግሎት/ 40/አርባ ቀናት፤ መሆኑን መገንዘብ አለበት።
 14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
 15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0582470509 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ

መንግስት በምሥ/ጎጃም ዞን

የሸበል በረንታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት