Mota Farmer's Cooperative Union

Be'kur Tir 17, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥ/ጎጃም ዞን የሞጣ የሁገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃላ.የተ. በአንድ ቦታ ላይ የሚሠሩ ሦስት ህንፃዎችን ማለትም መጋዘን፡የጥበቃ ቤትና መፀዳጃ ቤት፡ ተጀምረዉ የተቋረጡን የህንፃ ግንባታ ለማሠራት በማቀዱ ሙሉ የሰዉ ኃይል ጉልበት፣ የግንባታ ቁሳቁስ ማለትም እንደ የጣራ ብረት መሥቀያ ክሬን ፡ሚክሠር ቫይብሬተር እና ሌሎች የመሣሠሉትን ማሽኖች እንዲሁም የግንባታ ጥሬ እቃዎችን አቅርቦት አሟልተዉ መወዳደርና መስራት የሚፈልጉ የሀገር ዉሥጥ ተቋራጮችን በመጋበዝ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ በመሆኑ ግብዣዉን ያቀርባል፡፡

 1. ለ2013ዓ.ም የታደሰ፡የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት፣የንግድ ፈቃድና፡ እንዲሁም የንግድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (የቲን ቁጥር) ፡የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቫት ሠርተፊኬት)፤ 6 ወራት ያላለፈዉ የቫት ክሊራንሥ፡ የዘመኑን ግብር ሥለመገበራቸዉ የሚያሳይ የግብር ክሊራንስ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉሥጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. በዚህ ግንባታ መሳተፍ የሚችሉት ተቋራጮች ደረጃ- ጂ.ሲ 7 ወይም ጂ.ሲ/ቢ.ሲ 6 እና ከዚያ በላይ መሆናቸዉን እናስታዉቃለን፡፡
 3. የግዥዉ መጠን ከብር 100,000.00/አንድ መቶ ሽህ ብር / በላይ በመሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር በሁለት ኮፒ አያይዘዉ በማሸግ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡በተጨማሪም የእነዚሁኑ ኦርጂናል ማስረጃዎች ባለቤት/ስራ አስኪያጅ ወይም ወኪሎች ጨረታዉ ሢከፈት ኦርጂናል ማስረጃዎችን ወኪሎቹም ከሆኑ ኦርጂናል ዉክልናቸዉን ጭምር በአካል በእጃቸዉ ይዘዉ በመቅረብ ለጨረታ ኮሚቴዉ ማስመርመር አለባቸዉ፡፡
 5. በዉክልና የሚጫረቱ ተጫራቾች ግልፅና የማያሻማ ዉክልና ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ሆኖም የጨረታ ኮሚቴዉ በዉክልናዉ ላይ Tir ጣሬ ካደረበት ተጨማሪ ማስረጃ ሊጠይቅ ወይም ሊያጣራ ይችላል፡፡
 6. በጨረታዉ አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠዉ ተጫራች ባቀረበዉ የስራ ዝርዝር መሰረት ሦስቱንም ህንፃዎች በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ነዉ፡፡ አንድም ዋጋ አለመሙላት ከጨረታዉ ዉድድር ዉጭ ያደርጋል፡፡
 7. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 3 ከዩኒዬኑ ገ/ያዥ ማግኘት ይቻላል፡፡
 8. ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የግንባታ ዘርፍ ግዥ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ/በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞጣ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ሥም ማስያዝና ኦርጂናል ሲ.ፒ.ኦዉን በኦርጂናሉ የጨረታ ሠነድ ዉሥጥ ኮፒዉን ደግሞ በኮፒዉ የጨረታ ሠነድ/ፖሥታ ዉሥጥ በማድረግ ማሸግ አለባቸዉ፡፡
 9. ማንኛዉም ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም ተመሳሳይ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ ምሥ/ጎጃም ዞን በሞጣ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ መግዛትና አሽገዉ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ቅዳሜ እስከ 6፡00 የስራ ቀን መሆኑ ይታወቅ፡፡
 10. ጨረታዉ በ21ኛዉ ቀን ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በምሥ/ጎጃም ዞን በሞጣ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን/ሃላ.የተ) ቢሮ ቁጥር 1/በ8፡00 ታሽጉ በ8፡30 ይከፈታል፡፡ተጫራቶች በራሳቸዉ ምክንያት ባይገኙና በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሡትን ኦርጂናል በእለቱ መታየት የሚገባቸዉን ማስረጃዎች ካላቀረቡ የጨረታ ፖስታቸዉ እንደማይከፈትና አሟልተዉ የተገኙት ተጫራቾች ፖስታዎች ብቻ እንዲከፈት በማድረግ ዉድድሩ ይካሄዳል፡፡
 11. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተቋራጮች የዉል ማስከበሪያ የሥራዉን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ /በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
 12. ዩኒዬኑ በግንባታዎቹ ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ የተሻለ ዘዴ ካገኘም ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
 13. በማስታወቂያዉ ያልተገለጹ ነገሮች ቢኖሩ ዩኒዬኑ ባወጣዉ የጨረታ መመሪያዉ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ፡፡
 14. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ሞጣ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0586610266/ ፋክስ ቁጥር 0586611687 በመደወልና በመላክ ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የሞጣ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ማህበራት ዩኒዬን ኃላ.የተ.