በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስደ/ወሎ/ዞን የወረባቦ ወረዳ ግዥ/ን/አስ/ቡድን አጠቃላይ መሰናዶ ትምህርት ቤት አገልግሎት የሚውል ኣስር መማሪያ ክፍል የያዘ G + 1 ግንባታ ስራ GC- 5 /BC-5/ እና ከዛ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ግንባታውን ማሰራት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ስደ/ወሎ/ዞን የወረባቦ ወረዳ ግዥ/ን/አስ/ቡድን በአልማ በጀት ድጋፍ በ2012ዓም ለወረባቦ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በቢስቲማ ከተማ አጠቃላይ መሰናዶ ትምህርት ቤት አገልግሎት የሚውል ኣስር መማሪያ ክፍል የያዘ G + 1 ግንባታ ስራ GC- 5 /BC-5/ እና ከዛ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ግንባታውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ የሚከተለትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ 

 1. ተጫራቶች በዘርፉ አግባብ ያለው ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የሙያ ብቃትና ደረጃ የሚያቀርቡና ትከክለኛኮፒ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
 3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
 4. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: የሚቀርበው ፎቶ ኮፒ የሚነበብ መሆን አለበት:: 
 5. ተጫራቾች የቀረበላቸውን የጨረታ መመሪያ በአግባቡ ማንበብና ዋጋቸውን በነጻ ገበያ ዋጋ በመሙላት ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ እትም ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 ከረዳት ገንዘብ ያዥ መግዛት/ማግኘት ይቻላል፡፡ 
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደርበት ጥቅል ዋጋ ድምር 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ፡ በመቁረጥ ደረሰኙን አብረው አሽገው ማስገባት ይኖርበታል ፡፡ የሚያዘው ዋስትና ለዘጠና የስራ ቀንና በላይ የሚያገለግል መሆን አለበት፡፡ 
 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በሁለት ፖስታ በማዘጋጀት ኦርጂናልና ኮፒ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በወረባቦ ወረዳ ግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 22ኛው ቀን 3፡59ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 9. የጨረታው አሸናፊተወዳዳሪ ድርጅት የሚለየው በዝቅተኛ ዋጋ ላይ በመመስረት ሲሆን የግንባታው ስራ 240 የስራ ቀን ይወስዳል፡፡ 
 10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረባቦ ወረዳ በግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 በ22ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መከፈቻ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ እና የህዝብ የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢኖሩም ባይኖሩም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም፡፡ 
 11. አሸናፊ ተጫራች አስፈላጊውን የሰው ሀይል ና የግንባታ እቃ ለማሟላት በቀረበው የስራ ዝርዝር መሰረት የግንባታ ስራውን በመስራት ከባለሙያ የክፍያ ትእዛዝ በመያዝ ክፍያ መውሰድ አለበት፡፡ 
 12. ከመሀንዲስ ግምት 20% በታች ዝቅ ብለው ለሚገቡ ስራ ተቋራጮች ከ20% በታች ላለው ለእያንዳንዱ አንድ ፐርሰንት እጥፍ ሁለት ፐርሰንት ከ 10% ላይ ደምረው የወል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡ 
 13. አሸናፊው አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ መጥቶ ከባለ በጀት መስሪያቤቱ ጋር ውል መውሰድ አለበት፡፡ 
 14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 15. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ወረባቦ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0332210025 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ማብራሪያ መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 

በደ/ወሎ/ዞን የወረባቦ ወረዳ 

ግዥ/ን/አስ/ቡድን