Bichena City Administration Finance and Economic Development Bureau, የብቸና ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

Addis Zemen

የግልፅ ጨረታ 

ማስታወቂያ ቁጥር 5 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን የብቸና ከተማ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ ዕቃዎች ግዥ ማለትም:- 

 • ሎት- 1 የድምፅና ምስል መቅረጽ ዕቃዎች ግዥ፣
 • ሎት -2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣
 • ሎት- 3 የጀነሬተርና የጀነኔተር ዕቃዎች ግዥ፣ 
 • ሎት- 4 የህንፃ መሳሪያ ዕቃዎች ግዥ፣
 • ሎት- 5 የሞተር ብስክሌት ጎማና መለዋወጫ ዕቃዎች ግዥ፣
 • ሎት- 8 የውጭ ሀገር የሚሰሩ የቤትና የቢሮ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። 

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቶች በጨረታው እንድትሳተፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን:: 

ዝርዝር መረጃውንም በጨረታ ሰነዱ ተካቷል።

በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ 
 2. የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው፣ 
 3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው። 
 4. ተጫራቾች በጫረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለሎት 1፤3፤4፤5 ላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ግዥ የጫረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 30/ሰላሳ ብር እና ለሎት 2 እና ሎት 6 ለእያንዳንዱ ለተጠቀሰው የግዥ ዓይነት የጫረታ ሰነድ የማይመለስ 50 ብር /ሀምሳ ብር በመክፈል ጫረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የብቸና ከተማ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ። 
 6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 3፤4፤5 ላይ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ግዥ 1000 ብር/አንድ ሺህ /1 ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 እና 6 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ ግዥ 2000 ብር ሁለት ሺህ ብር ለሎት 2 ደግሞ 4000 ብር/አራት ሺህ ብር/በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ህጋዊ የገቢ ደረሰኝ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው:: 
 7. ተጫራቶች ለሁሉም ሎቶች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ስስም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቶች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው ሲከፈት ተጫራቾች/ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት ኢያስተጓጉልም። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በማስታወቂያው በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል። 
 8. የጨረታ አሸናፊዎች የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተገለፀላቸው 5/አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 /አምስት በተከታታይ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና በጫረታ ያሸነፉበትን የመወዳደሪያ ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ህጋዊ የገቢ ደረሰኝ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማቅረብ ከብ/ከ/አስ/ከ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ጋር እስፈላጊውን የውል ስምምነት መፈፀም ኣለባቸው፡፡ 
 9. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆኑ ነገሮች መኖር የለበትም ካለ ተጫራቹ ፓራፍ ማድረግ አለበት። በጨረታ ሰነዱ ላይ ና በፖስታው ላይ የተጫራች ድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት። 
 10. በሁሉም ሎቶች ላይ የሚቀርቡ ዕቃዎችን አሸናፊው ድርጅት ንብረት ማስቀመጫ መጋዘን ድረስ ሙሉ ወጪ ለመሸፈንና በማቅረብ የማስረከብ ግዴታ ያለበት ሲሆን እንዲሁም እያንዳንዱን ዕቃ በቀረበው ሞዴል መሰረት በባለሙያ እያረጋገጥን የምንረከብ ይሆናል። 
 11. ለሁሉም ሎቶች መስሪያ ቤቱ አሸናፊ የሚለየው በሎት ድምር በሞሉት ዝቅተኛዋጋ መሆኑ መታወቅ አለበት። ተጫራቶች በየሎቱ ምድብ የቀረቡትን ዝርዝር ዕቃዎች የመወዳደሪያ ዋጋሙሉ በሙሉ መሙላት አለባቸው። እያንዳንዱን የዕቃ ዝርዝር ነጠላ ዋጋ ሙሉ በሙሉ ካልሞሉ ከጫራታ ውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡ 
 12. ከሎት 1 እስከ 6 ላሉ የሎት ምድቦች ጽ/ቤቱ የጫራታ አሸናፊ ከሆነው ተጫራች የጫራታ ይዘቱ ላይቀየር ከዕቃው ጠቅላላ ዋጋl መጠን ላይ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል። 
 13. ስለ ጨረታው አጠቃላይ መረጃ ከጨረታ ሰነዱና ከተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት መመልከት ይችላሉ። 
 14. ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ አስፈላጊ ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይችላሉ፡፡ 
 15. የጫረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች በአቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም። 
 16. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጫረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 17. ለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር /0586651445/0586651446 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

የብቸና ከተማ 

አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት