Kirkos Sub City Administration Land Development And Management Bureau

Addis Zemen Tir 27, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት /ቤት እና በስራ አስኪያጅ /ቤት የግዥ//አስ// አገልግሎት ደጋፊ የስራ ሂደት ለተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚውል፡፡

 • ሎት 1 ደንብ ልብስ
 • ሎት 2 አላቂ የጽ/መሳሪያ
 • ሎት 3 ህትመት
 • ሎት 4 አላቂ የፅዳት እቃዎች
 • ሎት5 የመኪና ጎማ ከመነዳሪ የመኪና ውስጥ እቃዎችና ተያያዥ
 • ሎት 6 የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች
 • ሎት 7 የስቶር መደርደሪያ የብረት

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

 1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ቲን ማቅረብ የሚችል፣ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ
 2. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100/አንድ መቶ ብር / ብቻ በመከፈል የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት 230 እስከ 1100 በመሬት ልማትና ማኔጅመንት /ቤት በግዥ//አስደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 መግዛት ይችላሉ፡፡
 3. የጨረታ ማስከበሪያ 1ኛሎት 1 ደንብ ልብስ ብር 3000.00 2ኛሎት 2 አላቂ የጽ/መሳሪያዎች ብር 2000,00 3 ሎት 3 ህትመት ብር 4000.00 4 ሎት 4 አላቂ የፅዳት እቃዎች ብር 3000.00 5ኛሎት 5 የመኪና ጎማ ከመነዳሪ የመኪና ውስጥ እቃዎችና ተያያዥ ብር 8,000.00 6. ሎት 6 የኮምፒውተር ተዛማጅ እቃዎች ብር 4000.00
 4.  7ኛሎት 7 የስቶር መደርደሪያ የብረት ብር 5000.00በባንክ በተመሰከረለት /CPO/ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።
 5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ዶክመንት በተለያየ ስታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ቀን ድረስ በቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 6. ተጫራቾች በሚያቀርቡት እቃዎች ናሙና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት መቅረብ አለበት፡፡
 7. ጨረታው 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ተዘግቶ ተጫራቾች ባሉበት ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 10ኛው ቀን 430 መሬት ልማትና ማኔጅመንት /ቤት በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
 8. ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ /ቤቱ እስከ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 9. ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው
 10.  /ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት

ስልክ ቁጥር፡– 011-558-00-40 ወይም 011-854-57-12 መደወል ይችላሉ

አድራሻ ከእስጢፋኖስ ወደ 22 በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ አጠገብ በሚገኘው አዲሱ ቢሮ መሬት ልማትና ማኔጅመንት /ቤት ቢሮ ቁጥር 30

 

የቂርቆስ /ከተማ መሬት ልማትና ማኔጅመንት

/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ

አገልግሎት ደጋፊ የሥራ ሂደት