• Pending

Hirenzi Special Secondary School

Addis Zemen መስከረም21፣2013

የጨረታ ማስታወቂያ

በስልጤ ልማት ማህበር የሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 2013 በጀት አመት ተቀብሎ ለሚያስተምራቸው እስከ 460 ለሚደርሱ ተማሪዎች ቀለብ አገልግሎት የሚውል

 • የባልትና ዕቃዎች፣ ጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ፣ ዳቦ፣ የጤፍ ዱቄት፣ ስጋ እና
 • የማገዶ እንጨት እንዲሁም
 • ለከብቶች እና ለዶሮ እርባታ ማዕከል የሚያስፈልጉ የተለያዩ መኖዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለአቅራቢዎች መስጠት ይፈልጋል

የዕቃዎቹ ዝርዝር የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ CPO መጠን

 1. ለጥራጥሬ፣ የምግብ ሸቀጣሸቀጥ እና የባልትና ዕቃዎችብር 5000.00
 2. ለዳቦ ብር 2000.00
 3. የጤፍ ዱቄት ብር 5000.00
 4. ለሙስሊም ጥሬ ስጋብር 2000.00
 5. ለማገዶ እንጨት ብር 1000.00
 6. የከብቶች እና የዶሮ መኖብር 1000.00

በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡

 1. በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፍቃድና የስራ ልምድ ያላቸው
 2. የዘመኑን የሥራ ግብር ከፍለው ያጠናቀቁ
 3. የቲን ቁጥር ያላቸው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 4. የቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(ቢድ ቦንድ) በሚወዳደሩበት ዕቃ በተጠየቀው መጠን ማስያዝ አለባቸው
 6. አሸናፊ የሆነ ድርጅት ንብረቱን እስከ ሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት በውሉ መሰረት ማቅረብ የሚችል
 7.  ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ከሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 8. ከአንድ በላይ በሆኑ ዕቃዎች የሚወዳደር አቅራቢ በእያንዳንዱ በሚወዳደርባቸው ዕቃዎች የተጠየቀውን CPO ማስያዝ ይኖርበታል።
 9. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 430 በሀይረንዚ ልዩ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 10.  ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው
 11. ተጫራቾች ሆኑ ወኪሎቻቸው ጨረታው ሲከፈት ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የሚያስቀረው ነገር ሊኖር አይችልም
 12. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467710462 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በስልጤ ልማት ማህበር የሀይረንዚ ልዩ 2 ደረጃ /ቤት