Sidama National Government TVET Science technology office

Addis Zemen Tir 26, 2013

 የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 36/13

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቴክ////ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ 2013 በጀት ዓመት በአለታ ወንዶ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ሊያሠራ ላቀደው

 • የድጋፍ ግንብ ( Retaining Wal) እና
 • አዳራሽ መድረክ ግንባታ ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

 1. ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተጫራቾች 2013 / ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው መንግሥት ተቋም የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ(VAT) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
 2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣የሥራ መሳሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
 3. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሰርቶ ለማስረከብ ከአሰሪ እና ከሚመለከታቸው መሥርያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፣
 4.  የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ)  መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፡፡ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
 5.  የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና(bid security) 25,000.00 / ሃያ አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
 6.  የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ህጋዊ ፈቃዳቸውንና .. (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 21(ሃያ አንድ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00(ሦስት መቶ ብር) በሲዳ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቴክ/// ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ ፋይናንስ ክፍል በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ::
 7.  የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው::
 8. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 እስከ 600 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የቴክ////ሳይንስና ቴከኖሎጂ ቢሮ ግዥ/ንብ ኬዝ ቲም 11 ቁጥር ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሽግ አለበት፡፡
 9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 600 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 800 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም::
 10. አሠሪው /ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

አድራሻ፡ሃዋሳ መስቀል አደባባይ ፊት ለፊት መናኸሪያ ሌዊ ሆቴል እና ከላዊዝ ስታር ሆቴል መካከል ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0462121109

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

የቴክ////ሳይንስና ቴክኖሎጂ ቢሮ

ሃዋሳ ከተማ