ANRS North Shoa Angolelana Tera Woreda Animal Resource Development Accountable Bureau

Addis Zemen Tir 23, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ግዥ ፈጻሚው መ/ቤት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የአን/ጠራ ወረዳ እን/ሃ/ል/ተ/ፅ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

 1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር /ቲን/ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቲን/ የተመዘገበ የምስክር ወረቀት ዋናውን ና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችል
 2. ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
 3. የጨረታ ሰነዱን ገዝተው ሞልተው መፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማቅረብ እለባቸው።
 4. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ሞልተው በመፈረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንከ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ሰገኢ/ት/ዋ/ፅ/ቤት በመሂ1(አንድ) 1 % የተያዘበትን ደረሰኝ በኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት፡ በጠቅላላ የሰነዱን ኮፒዎች ለብቻው በሌላ ፖስታ በማሸግ የተያዘበትን ማስረጃ በጥንቃቄ በማሸግ የግዥ ፈጻሚው መ/ቤቱን የተጫራቾችን ስምና አድራሻ እንዲሁም የግዥውን የእቃ አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ጨረታው በዚሁ እለት በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም) በጽ/ ቤቱ ቁጥር 12 ይከፈታል።
 6.  16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
 7. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 10,000/አስር ሺህ እና ለአገልግሎት ከብር 3000/ ሶስት ሽህ ብር/ በላይ ለሚሆነው ግዥዎች ኣቅራቢው ከሚፈጸምለት ከፍያ ላይ 2% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
 8. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ ጽ/ቤታችን ተጠያቂ አይሆንም፡፡
 9. አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈበትን መድሃኒቶቹን በራሱ ትራንስፖርት አንጎለላና ጠራ ወረዳ ጫጫ እንስሳት ሃብት ፅ/ቤት ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
 10. ማንኛውም የመድሃኒት አይነት የአገልግሎት ጊዜው 2 ዓመት ከዚያ በላይ መሆን አለበት
 11. . ተጫራቾች በጨረታው የአፈጻጸም ሂደት ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ አንቀጽ 56፡57 እና 38 እንዲሁም በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 በአንቀጽ 39 መሰረት አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 12. ማንኛውም ኮፒ የሚያረጉ ማስረጃዎች በትከከል መነበብና መታየት እለባቸው፡፡
 13. . ተጫራቾች በሞሎት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍለድ መደለዝ እይፈቀድም
 14. . አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱን ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኃላ ውል ለመግባት ፈቃደኛ የሆነ፡፡
 15. ተጫራቾች የመድሃኒቱን በአይነትም ሆነ መጠን በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የመድሃኒት አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችለም፡፡
 16. የውል ማስከበሪያ ከአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው ከተዋዋሉት መድሃኒቶች አንድ እንኳ ቢጎድል ያስያዙት የውል ማስከበሪያ በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናል።
 17. አንድ ተጫራች ሌላው የሚያቀርበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
 18. መ/ቤቱ የሚፈጸመው የግዥ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% የመቀነስም የመጨመርም መብት አለው
 19. የጨረታ ሰነዱ ከወረዳው ኢ/ል/ዋ/ፅ/ቤት የማይመለስ ብር 30 በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመግዛት መጫረት ይቻላል
 20. . መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
 21. በሰንጠረ ላይ ከተቀመጠው ማብራሪያ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም፡፡
 22. ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት በደሴ መስመር ላይ ነው
 23. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 01 163204 12 ደውለው ይጠይቁ፡፡

በአብክመ የእንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ

ኤጀንሲ ሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎስሳና ጠራ ወረዳ ያአን/ሀ//ተ/ፅ/ቤት