North Shewa zone Moja and Wedera Woreda Health Office Gawona Health Care Center

Be'kur ጥቅምት23፣2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ በሚገኘው የጋውና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለ2013 በጀት አመት

 • ለተለያዩ የግንባታ አይነቶች የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን፣
 • የግንባታ የአጥር ስራ፣ የቢሮ እቃ፣
 • የጽዳት፣ የህትመት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
 • የኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣
 • የጀኔሬተር ጥገና ፣የሞተር ጥገና ለድጋፍ ሰጭ እና ለባለሙያተኞች የደንብ ልብስ በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር

የምትችሉ ሲሆን፡-

 1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
 2. የግዥ መጠን 50000/ሃምሳ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
 3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እናይጠቅመኛል የሚሉትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. በግንባታ ዘርፍ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ከደረጃ /6/ በላይ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. የእቃዎችን እና የግንባታ አይነት ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 6. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ግዥ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ወይም የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታለስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል 16ኛው ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
 9. በጥንቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ድጋፍይደረግላቸዋል፡፡
 10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው፡፡
 11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 033 89948 60/09 20 86 72 19 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 12. የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
 • አድራሻ፡- በአክብመ የሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 100 ኪ.ሜ ወደ ደሴ መስመርከሚወስደው መንገድ ጣርማ በር ዋሻ ወደ ምዕራብ በ40 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ነው፡፡
 • የጋውና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ