Gimibi City FEDB Bureau

Addis Zemen ነሐሴ13፣2012

የጨረታ ማስታወቂያ 

በምዕራብ ወለጋ ዞን የጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮት/ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት ለጊምቢ ከተማ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። 

 • የጽሕፈት መሣሪያዎች 
 • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡
 • የተለያዩ ፈርኒቸሮች 
 • የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣
 • የስፖርት ቱታና ስኒከር ጫማ የተለያዩ የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማዎች 

ተጫራቾች ማሟላት ያስባቸው 

 1. በየዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2012 የመንግስት ግብርና ታክስ ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ። 
 2. ማንኛውም ተወዳዳሪ ቫት ተመዝጋቢ ሆኖ ቲን (የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር) ማቅረብ አለበት። 
 3. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር ለጊምቢ ከተማ ገቢዎች ባለስልጣን ገቢ አድርጎ ሰነዱን ከጊምቢ  ከተማ ገ/ኢኮ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም ግዥና ንብረት ዘርፍ አስተዳደር ክፍል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ ጠዋት ከ2:30 – 6:30 ከሰዓት በኋላ ከ7:30 -11:30 በመግዛት ሞልተው ማስገባት ይችላሉ። 
 4. የጨረታ ማስከበሪያ 2% (ሁለት ፐርሰንት) ጊምቢ ከተማ ውስጥ  በሚገኘው በማንኛውም ባንክ ቅርንጫፍ በCPO አስገብቶ ማስረጃ  ማቅረብ የሚችል። 
 5. የጨረታ አሸናፊ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% (አስር ፐርሰንት) ህጋዊ ሰነድ  (በባንክ የተረጋገጠ) ማስረጃ ማቅረብ አለበት። 
 6. ተወዳዳሪዎች ስርዝ ድልዝ የሌለውን የጨረታ ሰነድ ሞልቶ  ዶክመንቱን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በተለያየ ካኪ ፖስታ ውስጥ  አሽጎ ሀላፊነት ባለው ሰው በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና ማህተም  ከተደረገ በኋላ ማቅረብ ይኖርበታል። 
 7. አሸናፊው ያሸነፈበትን አቅርቦት በውሉ መሠረት በጊምቢ ከተማ  ገ/ኢ/ትብብር/ጽ/ቤት በጊዜ ማቅረብ የሚችል። 
 8. ተጫራቶች ሰነዱ ከተከፈተ በኋላ የዋጋማሻሻያ ማድረግ አይችሉም። 
 9. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ዕቃ ለናሙና ማቅረብ የሚችል። 
 10. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ለማደናቀፍ ከሞከረ ከጨረታ  ውጪ ሆኖ ለወደፊት በማንኛውም የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል። 
 11. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15  (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ  በ16ኛው (በአስራ ስድስተኛው) የስራ ቀን በጊምቢ ከተማ ገንዘብና  ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ከጠዋቱ 4:00 ላይ የጨረታው ሳጥን  ተዘግተው በ4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች  ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል። 

ማሳሰቢያ:- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ  ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። 

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር:-057-771-1783 ደውለው  መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

በምዕራብ ወለጋ ዞን የጊምቢ ከተማ ገንዘብና ኢኮ/ት/ጽ/ቤት