Abreha Weasbeha Secondary School

Be'kur ሰኔ8፣2012

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ጎጃም ዞን እነ/ሣ/ም/ወረዳ መርጡ ለማርያም ቀበሌ 01 የአብ/ወ/አፅ/አጠ/መሰ/2ኛ/ደ/ት/ቤት የመማሪያ ክፍል(G+1) ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት የሚከተለውን መስፈርት የሚያሟሉ

ተቋራጮች መጫረት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

 1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/ቲን/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 4. የሚጫረቱበት ጥቅል ዋጋ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 11፡00 ድረስ በአብ/ወ/አ/አጠ/መሰ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ከተጫራቾች መመሪያ ጋር የጨረታ ሰነዱን 100 ብር መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ግንባታ ስራ በሚያቀርቡበት ዋጋ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ በማካተት ጨረታ ሰነዱ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የድርጅቱን ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማና ማህተም ማድረግና የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በማሸግ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግና ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በሙሉ በማጠቃቀል ፖስታው ላይ በመጥቀስ በአብ/ወ/ፅ/አጠ/መሰ/2ኛ/ደ/ት/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ጨረታው ከ08/10/2012 ዓ/ም እስከ 21/10/2012 ዓ/ም ድረስ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ማስገባት የሚችሉና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባይገኙም/ ታሽጐ በ22/10/2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ያላቸውን አስተያየት የጨረታ ቀኑ ከማለቁ ከ1 ቀን በፊት ለት/ቤቱ አቤቱታቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ ብር የጠቅላላ ዋጋውን 1 በመቶ ሆኖ የቫት ተመዝጋቢ ተወዳዳሪ ከሆኑ በሚይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከነቫቱ መሆኑንና እንደተጫራች ምርጫ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/በጥሬ ገንዘብ/ በመሂ-1 ገቢ አድርጎ ደረሰኙን ማስያዝ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍክሬዲት ወይም ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መኖር ይኖርበታል፡፡
 10. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ካለ ከጨረታው ውጭ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
 11. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት ወይም በጥቅል ዝቅተኛ ዋጋ ከሞሉት ይሆናል፡፡
 12. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 13. የስራው ጥራት በባለሙያ ተረጋግጦ የክፍያ ትዕዛዝ ሲደርሰን ክፍያ የምንፈፅም መሆኑን እናሣስባለን፡፡
 14. የባለሙያ የዕጅ ዋጋ የግንባታውን አጠቃላይ ቁሣቁስ፣ ውሃ ማጠጣትና አቅርቦት ሌሎች ወጭዎችን አሸናፊ ድርጅቱ የሚሸፍን ወጭ ጨምሮ መወዳደር ይጠበቅበታል፡፡
 15. በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በተጨማሪ መረጃ ቢፈልጉ በእነ/ሣ/ም/ወ/ት/ጽ/ቤት በአብ/ወ/አፅ/አጠ/መሰ/2ኛ/ደ/ት/ቤት ስልክ ቁጥር 0586660002/0946780627 በመደወል እና በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 16. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ከተገለፀው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት በኋላ ውስጥ ጨረታ አሸናፊው በውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ አለበት፡፡
 17.  አጠቃላይ ወጭ ቁሣቁስ የጉልበት ዋጋ፣ ውሃ ማጠጣት እንዲሁም ሌሎች ተጫራቾች የሚሸፍኑ ሆኖ ጥሬ እቃዎች በጠራት ኮሚቴ እየተረጋገጡ ገቢ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
 18. ተጫራቾች የተቋራጭነት ደረጃ GC 5 በላይ የስራ ደረጃ ያለው መሆን አለበት፡፡
 19. ስራው በጽ/ቤቱ መሀንዲስ ቁጥጥር ይሆናል፡፡
 20. የቅድሚያ ክፍያ ዋስትና/30 በመቶ/ የሚለቀቀው በ3 ጊዜ ሆኖ ይህም የሚለቀቀውን ብር ያህል ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
 21. ዝርዝር ስራዎችን የሚፈልጉ ከሆነ በአብ/ወ/አፅ/አጠ/መሰ/2ኛ/ደ/ት/ቤት በአካል በመገኘት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 22. የማወዳደሪያ ሃሣብ ማቅረቢያ በአማረኛ ቋንቋ ነው፡፡
 23. በጨረታው የሚሣተፍ በግንባታ ስራ አገልግሎት ስራ ዘርፍ ቢያንስ አንድ ዓመትና በላይ ተመሣሣይ ስራ (G+0፣G+1) የሆነ መማሪያ ክፍል፤ ቤተ-መፅሀፍት፤ ቤተ-ሙከራ፣ አዳራሽ፤ የአስተዳደር ቢሮ) የሰሩ መሆን አለባቸው፡፡ ለዚህም ማስረጃ ከጨረታው ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 24. የክፍያ ሁኔታ በየግንባታው ደረጃ እየታየ የሚከፈል ሆኖ ስራው በባለሙያና በሃላፊ እየተረጋገጠ መከፈል እንዳለበት የሚያምን መሆን አለበት፡፡
 25. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሣብና ዋጋ ላይ ፊርማቸውን፣ ቀን የድርጅቱን ማህተም ማስፈር አለባቸው፡፡

የአብርሃ ወአፅብሃ አጠ/መሰ/2ኛ/ደ/ት/ቤት