• Gojjam

kinfaza Begela Woreda FEDB

Be'kur ነሐሴ4፣2012

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በስሩ ለሚተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2013 ዓ/ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት የተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ እቃዎችን ግዥ ለመፈፀም ብቁ ተወዳዳሪዎችን በግልጽ የጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ያላቸው፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣

ከላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት የምትችሉ ተወዳዳሪዎች ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱ በኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ማግኘት የሚቻል ሲሆን እያንዳንዱ በሎት በማይመለስ 50 ብር ብቻ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ብቻ በመግዛት መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቴክኒካል ኮፒ፣ ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ብሎ በመለየት በአንድ በታሸገ ኢንበሎፕ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚያቀርቡት የጠቅላላ ዋጋውን 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ በመቁረጥ ከዋናው ፋይናንሽያል ሰነድ ጋር መያያዝ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊ ድርጅቱ የውል ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ጨረታው በቀን —4፡00 ታሽጐ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 4፡30 በኪን/በገ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ላይ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመጨረሻው ቀን የመንግስት በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሣሣይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡

  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0900415924 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  • የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የኪንፋዝ በገላ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት