Defence Resource Management College

Addis Zemen Tahsas 2, 2013

በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መያ ቁጥር መከ/ሪሶ/ማኔ/ኮሌጅ ግጨ 03/2013

በሀገር መከላከያ ዩኒቨርስቲ ሪሶ/ማኔ ኮሌጅ ለ2013 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች እነዚህ እቃዎች ማለትም

 • አላቂ የቢሮ የፅህፈት እቃዎች፣
 • የትምህርት መርጃ እቃዎች፣
 • ሌሎች አላቂ የፅዳት እቃዎች፤
 • እና ልዩ ልዩ መሳሪያዎች፤
 • የፕላነት ማሽነሪ እና
 • ለመሳሪያ እድሳት ጥገና፤
 • የቢሮ ቋሚ እቃዎች የተዘረዘሩትን የተለያዩ የቢሮ መረጃ መሳሪያዎችን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትይፈልጋል፡፡
 1. ተጫራቶች አግባብ ያለው የዘመኑ ግብር የተከፈለበት እና የታክስ ንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. የመንግሥት ግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ላይ የተመዘገቡ እና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
 3. የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
 4. የመንግሥት ግዥ ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተለያዩ የቢሮ ፅህፈት እቃዎች፤ የትምህርት መርጃ እቃዎች፤ ሌሎች አላቂ የፅዳት እቃዎች እና ልዩልዩ የፕላነት ማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት ጥገና፤ የቢሮ ቋሚ እቃዎች አቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ላይ የተመዘገቡ እና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
 5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስረከቢያ ከነቫቱ ለሚያቀርቡት እቃ ጠ/ዋጋ 2% በማስያዝ የጨረታ ማስረከቢያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ጋራንቲ (90 ቀን) ማስያዝ አለበት፡፡
 6. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ ብር 50 (ሃምሳ ብር) የተዘጋጀው ሰነድ ክፍያ ፈፅመው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
 7. ሲፒኦ ሲዘጋጅ MOND UNIVERSITY RESOURCE MANAGEMENT COLLEGE በሚል ስም መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
 8. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የእቃዎች ዶክሜንቶችን ፋይናሻልና ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከታህሳስ 1 ቀን 2013 ዓም እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ማቅረብ አለባቸው፡፡
 9. ጨረታው ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለዚህ በተዘጋጀ ቢሮ በግልፅ ይከፈታል፡፡
 10. የመከላኪያ ዩኒቨርስቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 11. ናሙና ለሚያስፈልጋቸው (አላቂ የቢሮ የፅህፈት እቃዎች፣ የትምህርት መርጃ እቃዎች፣ ሌሎች አላቂ የፅዳት እቃዎች እና ልዩ ልዩ የቢሮ ቋሚ እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ስለ ናሙናው የሚገልፅ ዝርዝር ሰፔስፊኬሽን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • አድራሻ የመከላከያ ዩኒቨርስቲ ሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ (ቢሾፍቱ) ኢንጅነሪንግ ግቢ ብሎክ ቁጥር 03 ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10፤ ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቀጥር፡- 0910291532 እና 0911194702 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር መከላከያ ዩኒቨርስቲ

የሪሶርስ ማኔጅመንት ኮሌጅ ግዥ ቡድን ቢሾፍቱ