Ministry of Defense, West Command General Directorate

Addis Zemen Tir 21, 2013

የብሄራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ፡

 1. የተለያየ አይነት የስራ ልብስ ቱታ እና ኤርጌንዶ ጫማ ነቀምት ካምፕ የሚራገፍ
 2. የተለያዩ አይነት የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎች ነቀምት ዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ
 3. የተለያዩ አይነት የቢሮ የፅዳት እቃዎች ነቀምት ዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ
 4. የተለያዩ አይነት ቋሚ የእጅ መገልገያ ማቴሪያሎች ነቀምት ካምፕ የሚራገፍ
 5. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ነቀምት ዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ
 6. የተለያዩ አይነት የጀኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች ነቀምት ዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ
 7.  የተለያዩ ዓይነት ለቤቶች የግንባታ እቃዎች ጋምቤላ ኢታንግ የሚራገፍ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘመኑ ንግድፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የቫት ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚገልፅ ሠርተፍኬት እንዲሁም ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን ግብር መክፈሉንና በጨረታ እንዲሳተፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ከሚመለከተው መስሪያ ቤት የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችልና የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ነቀምቴ በሚገኘው የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት ይችላሉ፡፡

የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/

 1. የተለያዩ አይነት የስራ ልብስ ቱታ እና ኤርጌንዶ ጫማ ነቀምት ካምፕ የሚራገፍ ብር— 999.60
 2. የተለያዩ አይነት የቢሮ የፅህፈት መሳሪያዎች ነቀምት ዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ ብር- -9290.84
 3. የተለያዩ አይነት የቢሮ የፅዳት እቃዎች ነቀምት ዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ ብር 5,623.50
 4. የተለያዩ አይነት ቋሚ የእጅ መገልገያ ማቴሪያሎች ነቀምት ካምፕ የሚራገፍ ብር- –1,000,04
 5. የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች ነቀምት ዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ ብር 4,830.00
 6.  የተለያዩ አይነት የጀኔሬተር መለዋወጫ እቃዎች ነቀምት ዴዴሳ ካምፕ የሚራገፍ ብር 10,400.00
 7. የተለያዩ ዓይነት ለቤቶች የግንባታ እቃዎች ጋምቤላ ኢታንግ የሚራገፍ ብር 92,550.64 ጨረታው አርብ Yekatit 5/2013 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ጨረታው አርብ Yekatit 5/2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በነቀምቴ ከተማ ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የቀድሞ ወጋገን ሆቴል ውስጥ ይከፈታል፡፡ 
 • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • *ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 057 861 87 73/ 057 660 43 45
 • Fax 057 660 01 19 መደወል ይቻላል

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር

የምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

ነቀምት