• Amhara
  • Applications have closed

Sirinka City Sub District Municipality

Be'kur Tahsas 5, 2013

 

የከተማ ቦታ የጨረታ ማስታወቂያ

  1. የጨረታ ዙር አንደኛ በድጋሜ
  2. የጨረታው አይነት፡- መደበኛ
  3. የስሪንቃ ከተማ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት የከተማ መሬት ልማት ባንክ ቡድን የከተማን ቦታ በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ

በተዘረዘረው መሰረት ለንግድ የተደራጀ ቦታን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል :: በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ 05/04/2013 ዓ/ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 ብር /ሶስት መቶ ብር / በመክፈል የከተማ መሬት ልማት ባንክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት ዘወትር በስራ ሰአት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን ::

4. የቦታው ዝርዝር መረጃ

/

መለያ

ኮድ

የቦታው

በካ/

በቦታው የሚፈቀደው

የአገልግሎት አይነት

ው ት 

አካባቢ

ጨረታው የሚዘጋበት

 

ጨረታው

የሚከፈትበት

የመነሻ ዋጋ

የቦታው

ደረጃ

የህንፃው ከፍታ

ቀን

ሰዓት

ቀን

ሰዓት

1

01

270

ሁለ ገብ የንግድ ማዕከል

መሀል ከተማ

19/04/2013

1100

20/04/2013

300

200

1

G+3

2

02

360

የመኖሪያ ቤት

ገጂ

19/04/2013

1100

20/04/2013

300

80

1

6 ክላስ በላይ ቪላ ሰርቨስ በብሎኬት

  • ሀ. የህንጻዎቹ ከፍታ በሰንጠረጁ ላይ እንደተገለጸው ፤ G+3(ለሁለ ገብ የንግድ ማዕከል እና ከዚያ በላይ ሆኖ 60 በመቶኛ የቦታው ስፋት በግንባታ ይሸፈናል
  • ለ. የህንጻዎቹ ከፍታ በሰንጠረጁ ላይ እንደተገለጸው ፤ የመኖሪያ ቤት ቨላ ሰርቨስ በብሎኬት የሚገነባ እና ከዚያ በላይ ሆኖ 60 በመቶኛ የቦታው ስፋት በግንባታ ይሸፈናል

5. የጨረታ መነሻ የሊዝ ዋጋ የንግድ ለ1 ካ/ሜ 200 በኢትዮጵያ ብር የመኖሪያ ቤት 80 በኢትዮጵያ ብር

6. የሚፈለገው አነስተኛ የቅድሚያ ክፍያ መጠን አጠቃላይ ቦታውን ያሸነፈበት ዋጋ 10 በመቶኛ ይሆናል ::

7. የቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ የመጀመሪያ ክፍያ ከተከፈለበት ጀምሮ እስከ ሊዝ ዘመኑ ለንግድ 40 አመት መጨረሻ ለመኖሪያ 50 አመት

8. ተጫከራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ የገንዘብ ክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ የተጫረቱበትን የቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት 5 በመቶ ያላነሰ በስሪንቃ ከተማ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት ስም በማስያዝ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል ::

9. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለፁለት በ10 የስራ ቀናት ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ዋጋ ከ10 በመቶኛ ያላነሰ ቅድሚያ ክፍያ ወይም የቴክኒክ ፕሮፓዛሉ ላይ የተገለፀውን ቅድሚያ ክፍያ በመፈፅም ውል ይወስዳል :: በተጠቀሰው ቀንና በተጨማሪ በማስጠንቀቂያ በሚሰጠው ጊዜ 3 ቀን ውስጥ ያልቀረበ ከጨረታው ይሰረዛል :: አሸናፊ የሆነው ተጫራች የውል ግዴታውን ለመፈፅም የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በዝግ ሂሳብ ያስያዘው ገንዘብ የሚታሰብለት ይሆናል :: አሸናፊው ተጫራች በዚህ መመሪያ አንቀፅ 30 በተጠቀሰው ቀነ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ካልዋለ አሸናፊነቱ ይሰረዛል :: ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለስሪንቃ ንኡስ ማዘጋጃ ቤቱ ገቢ ይሆናል :: ሁለተኛና ሶስተኛ የወጡ ተጫራቾች 1ኛ የወጣው ተጫራች ያስገባውን ወይም ያሸናፊነት ዋጋ በመክፈል ለመውሰድ ከፈለገ እንደየ ደረጃቸው የጨረታ አሸናፊ ሁነው ውል እንዲወስዱ ይደረጋል ::

10. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ በመያዝ በየራሳቸው ፖስታ በፅሁፍ ተለይቶ ታሽጎ መቅረብ አለበት :: ኦርጂናልና ኮፒ ፖስታዎች በስቴፕላር በአንድ ላይ እንዲያያዙይደረጋል ::

11. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደልና በአሀዝ መሙላት ይኖርባቸዋል :: በፊደል እና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል::

12. አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም

13. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ከ 05/04/2013 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 19/04/2013 ከቀኑ 11፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ብቻ ይሆናል ::

14. ጨረታው የሚዘጋው 19/04/2013 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ይሆናል ::

15. ጨረታው የሚከፈትበት 20/04/2013 ዓ/ም ከጧቱ 3፡00 ይሆናል ::

16. ቦታዉን በአካል ተገኝቶ መጎብኝት ለሚፈልጉ ተጫራቾች 08/04/2013 ዓ.ም(ሀሙስ) እና 13/04/2013 /ማክሰኞ/ ከጠዋቱ ከ3፡30 ጀምሮ እስከ 5፡00 ድረስ ቦታው በሚገኝበት ስሪንቃ ንዑስ ማዘጋጃ ቤት በመገኘት የተቋሙ የጨረታ ኮሚቴ አባላት የሚያስጎበኙ ይሆናል::

17. ጨረታ የሚከፈትበትን ቀን በተመለከተ በተራ ቁጥር 4 ላይ በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሰረት በስሪንቃ ከተማ ን/ማ/ቤት ሁሉም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት ይሆናል::

18. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

19. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 0333300045 ወይም 0912966720 በመደወል መጠየቅ ይቻላል ::

የሲሪንቃ ከተማ ንኡስ ማዘጋጃ ቤት