Ethiopian Revenue and Custom Commission Mojo Customs Branch Office

Addis Zemen Tahsas 27, 2013

 

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

የተተው እቃዎች በግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ20/2013 ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስመጪዎችን በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 51፤ ንዑስ አንቀፅ 1 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ 160/201 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት እቃቸውን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው እቃዎቻቸው እንደተተው ተቆጥረዋል፡፡

ስለሆነም በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያለ ንብረቶች ሰለሚወገዱበት ሥርዓት በአወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም

 • ሲሊንደር፣
 • የህንፃ መሳሪያዎች፣
 • ኤርፍረሽነር እና ተባይ ማጥፊያ ወረቀቶች፣
 • የወለል ምንጣፍ፣ ማሽኖች፣ ጡብ፣
 • እና ሌሎች እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉናከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ

ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

 1. ተጫራቾች የእቃዎቹን ዝርዝር ፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀን 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
 2. ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው እቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው:: ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም እቃ ለመግዛት የ5% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
 3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተሸናፊ ተጫራቶች ያስያዙትን የ ሰጨረታ ማስከበሪያ አሽናፊው እንደታወቀ በ3 (ሶስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ፡ ኣሽነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል፡፡ ተጫራቶች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ETHIOPIAN CUSTOMAS COMMISSION MOD]O BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን የግል ባንክ ከሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርንጫፎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት፡፡
 4. የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቶች እያንዳንዱን እቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፣ የሞሉበት ሠነድ፣ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ጠዋት 4፡45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡
 5. የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም:
 6. ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:45 ታሽጐ። በዚህ ዕለት ጠዋት 5፡00 ላይ ተጫራቶቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል
 7. ማንኛውም በግልፅ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች በጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቶችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም
 8. ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጨረታውን ለማሸነፍ ሲል መደለያ የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ይወገዳል ፡፡ ጨረታው ከተካሄደ በኋላም ቢሆን ጨረታ አሸናፊው ጨረታውን ያሸነፈው ስህገ-ወጥ መንገድ መሆኑ ከተረጋገጠ የጨረታው ውጤት ይሰረዛል፡፡
 9. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የእቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም::
 10. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም::
 11. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል ፡፡
 12. የግልፅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ አለበት: ሲ5 (አምስት) ቀናት) ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል ፡፡ ያሸነፉት እቃም በድጋሚ ለጨረታ ሽያጭ ይቀርባል፡፡
 13. በተራቁጥር 12 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን እቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ እቃውን ያላነሳያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል ፡፡ ሆኖም እቃው በ2(ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
 14. አሸናፊው ተጫራች እቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሀሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡
 15. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን እቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው::
 16. ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ እቃዎችን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
 17. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 022-236-01-90 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን

የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት