Mencheno Halaban Farmers Cooperative Union Ltd

Addis Zemen Hidar 21, 2013

የደረቅ ጭነት ማመለሻ ጨረታ ቁጥር 001/2013

 የጨረታ ተሳታፊዎች ዝርዝር ግዴታዎች

ማንኛውም ተጫራች ከዚህ በታች በዝርዝር የተጠቀሱትን ግዴታዎች በትክከል አንብቦና ተረድቶ የዉረታውን ሰነድ መሙላት ይኖርበታል፡፡

 1.  ለጨረታው አሸናፊ ድርጅት በሚያጓጉዘው የአፈር ማዳበሪያ መጠን ለከሰት ለሚችል ማንኛውም ጉዳት የመድህን ዋስትና የመግዛትና ከውል በፊት የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል፡፡
 2. ማጓጓዝ ሂደት ወጪ ያደረገው የአፈር ማዳበሪያ በጠፋበት፣ ቢበላሽበትና ቢጎድልበት ወዲያው በሚተመነው ተመን መሠረት የመተካት ግዴታ አለበት፡፡
 3. አጓጓዥ ድርጅቱ የሚጭነውን የኤፈር ማዳበሪያ ዓይነት፣ መጠን እና ጥራት አጣርቶ ማስጫን አለበት፡፡ ተጭኖ የሄደ የአፈር ማዳበሪያ በጥራት ችግር ወይም በብልሽት ምክንያት ተረካቢ ጣቢያ/ቀበሌ ኤልረከብም ካለ በትራስፖርተሩ በራሱ ወጪ ተመላሽ ያደርጋል፡፡
 4. ጭነቱን በሚገቡት ውል መሠረት በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጓጉዞ የመጨረስ፣
 5. የተረከቡትን ንብረት ለማድረሳቸው ከተቀባይ ህጋዊ ማህተም ያረፈበትና በተቀባይ ፊርማ የተረጋገጠ ከዩንየኑ ወጪ በተደረገ የአፈር ማዳበሪያ ገቢ ደረሰኝ ብቻ ሰነድ የማቅረብ፣
 6. ጠንካራ፣ ብቁና አስተማማኝ መኪናዎችን በማሰማራት ሥራው ሳይቋረጥ በወቅቱ የማጓጓዝ እና የማጓጓዣ መኪኖችን ዝርዝር ከነታርጋቸው ቤፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የተረጋገጠ ማስረጃና የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም የተሽከርካሪው ሊብሬ በባንክ ብድር የተያዘ ከሆነ ከአበዳሪው ባንክ ደብዳቤ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህን የማያሟላ ድርጅት በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
 7. ተጫራቹ የአስፋልትና የጠጠር መንገድ ታሳቢ በማድረግ አንድ ኩንታል የኤፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የሚሰጠው ዋጋ እንደ አካባቢው የመንገድ አውታር ሁኔታ በአንድ ኩንታል ለአንድ ኪሎ ሜትር/በጣቢያው ጠቅላላ ኪሎ ሜትር ለአንድ ኩንታል ዋጋ በመስጠት ለሁሉም የማራገፊያ ጣቢያ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፡፡ ለአንድ ማራገፊያ ጣቢያ ወይም ለወረዳ በአማካይ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች በአማራጭነት የተቀመጡትን መነሻ ማዕከላዊ መጋዘናት ሀላባ ቁሊቶ፣ ሻሸመኔ፣ ናዝሬት/ በሶስቱም ገጾች ላይ ዋጋ የመስጠት ግዴታ ያለበት ሲሆን የአንዱን ብቻ ሞልቶ ሌላውን ከፍት ማድረግ አይችልም፡፡
 9. ተጫራቾች በሶስቱም ወረዳዎች የሰጡት ዋጋ በአመቱ ከሚጓጓዘው የማዳበሪያ መጠን ጋር ተባዝቶ በድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡
 10. ከአንድ ማእከላዊ መጋዘን/ከሀላባ ቁሊቶ፣ ከሻሸመኔ ወይም ከአዳማ ለሶስቱም ወረዳዎች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ለሶስቱም ማእከላዊ መጋዘኖች የተለያየ ተጫራች ወይም አንድ ተጫራች አሸናፊ ሊሆን ይችላል፡፡
 11. የእያንዳንዱን የማራገፊያ ጣቢያ የመንገድ ሁኔታ በቦታው በመገኘት በአግባቡ አጥንቶ ዋጋ መስጠት የተጫራቶች ኃላፊነት ነው:: የጨረታ ዋጋ ከተሰጠ በኋላ የመንገዱን ሁኔታ በሚመለከት የሚቀርብ ማንኛውም ጥያቄ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 12. በአንድ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ የአፈር ማዳበሪያ ዕጥረት ካጋጠመ አማራጭ ከተሰጠው ማዕከላዊ መጋዘን ከወደብ የተጓጓዘበት ሂሳብ እየተሰላ በመጨመርና መቀነስ የክፍያው ልዩነት ተሰልቶ የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡
 13. . በጨረታ የሚሳተፍ ማንኛውም ድርጅት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000/ሀምሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ “ለመንቼኖ የሀላባ ገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩንየን ኃላፊነቱ የተወሰነ (Mencheno Halaban Farmers Cooperative Lion Ltd)” በሚል አሰርቶ ከዋጋ ማወዳደሪያው ጋር ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 14. ለሥራኤፈጻጸም ዋስትና አሸናፊድርጅቶች በሚያጓጉዙት የአፈር ማዳበሪያ መጠን ተሰልቶ ለማጓጓዣ ከሚከፈለው ገንዘብ በቅድሚያ2% ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ግለመንጽኖ የላባ ገበሬዎች ኅብረት ስራ ዩንየን ኃላፊነቱ የተወሰነ (Mencheno Baaban Farmers Cooperative union Ltd)” በሚል አሰርተው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 15. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሰጥቶ ባሸነፈባቸውጣቢያዎች ውል ከፈፀመበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10  ቀናት ውስጥ የማይጀምር ከሆነ ያስያዘው ሲፒኦ /CPO/ አይመለስለትም፡፡
 16. ተጫራቹ በአሸነፈበት ቦታሥራውን ለመስራት ውል ከፈፀመ በኋላ በተለያየ ምክንያትሥራውን ቢያቋርጥ ወይም ሥራውን ቢያጓትት ለሥራ አፈፃፀም ያስያዘው 2% ሲፒኦ /CPO/ እና ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ /CPO/ አይመለስለትም፡፡
 17. ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት የአፈር ማዳበሪያ ማዕከላዊ መጋዘን ጭኖ ከመነሳቱ በፊት በዩኒዮኑ እና በየወረዳው ካሉ ሥራው የሚመለከታቸው ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር መረጃ በመለዋወጥ ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ በየጊዜው ቀድሞ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡
 18. . ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት ዩንየኑ/ወረዳዎች በሚሰጡት የማራገፊያ ጣቢያዎች ቅደም ተከተል መሠረት በሁሉም ጣቢያዎች አጓጉዞ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡ በተሰጠውቅደምተከተል የማያደርስ የትራንስፖርት ድርጅትግን ለሚከሰተውችግር ተጠያቂይሆናል፡፡
 19. ማንኛወም በጨረታው አሸናፊ የሆነ የትራንስፖርት ድርጅት የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ ከዩኒየኑ ጋር የውል ስምምነት በመፈፀም ሥራውን ያከናውናል፡፡

2.የዩኒያኑ ግዴታ

1 የአፈር ማዳበሪያው በወቅቱ በሚፈለግበት ቦታ መድረሱንና ተቀባይ አካል ለመቀበሉ ማስረጃ መቅረቡን በማረጋገጥና ማጣራት የሚገባውን በፍጥነት አጣርቶ ከፍያውን ወዲያውኑ የመፈፀም፣

2. ከውል ተቀባይ በሚሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በመኪኖች የመጫን ችሎታ መጠን በፍጥነት መጫን፣

3. በማራገፊያ ጣቢያዎች የአፈር ማዳበሪያ ተጭኖ ከደረሰ በኋላ ፈጥኖ እንዲራገፍ ከሚመለከተው አካል በመነጋገር አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት፣

4. የአፈር ማዳበሪያ ወደ ማራገፊያ ጣቢያዎች ጭነው የሄዱ ተሽከርካሪዎች ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ካልሆነ በስተቀር ያለአግባብ ከሁለት ቀናትና ከዚያ በላይ ሳይራገፉ ከቆዩ በትራንስፖርት ሕግ መሠረት ሳያራግፍ የቆየው አካልዲመሬጅ እንዲከፍል የማስደረግ፣

5. የመጫንና የማራገፍ ሥራው ቀልጣፋ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር፣

 ማሳሰቢያ

 • ዋጋ የሚቀርብበት የጨረታ ሰነድ የዩንዮኑ ማህተም ከሌለስት ተቀባይነት የለውም፡፡
 • በጨረታው የሚወዳደሩድርጅቶች የጨረታው ሰነድ የውሉ አካል ሆኖ እንዲያገለግል ለራሳቸው ኮፒ አድርገው በማስቀረት ግዴታውን ጨምሮ በሁሉም ገጽ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
 • የአፈር ማዳበሪያ ተጠቃሚ ጣቢያዎች እና ወረዳዎች የአጠቃቀም ሁኔታ ወይም ደረጃ ዝርዝሩ ተያይዞ ቀርቧል፡፡
 • የማድረሻትራንስፖርት ዋጋ የሚሞላው ከዩንዮኑ በተሰጠው የጨረታ ሰነድ ላይ ሆኖ የትራንስፖርት ድርጅቱ ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ መደረግ ይኖርበታል፡፡
 • የአንዳንድ ማራገፊያ ጣቢያዎች ለውጥ ሊኖር እንደሚችል ይታወቅ፡፡

በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በሃሳባ ዞን መንቼኖ ሃባ ገ/ህ/ስራ ዩኒየን ሃ/የተወሰነ