Merekeb Farmers' Cooperative Union

Be'kur Tahsas 19, 2013

የሰብል ማጓጓዝ አገልግሎት ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ

መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ.የተ 197,050.00 ኩ/ል ሰብል የማጓጓዝ አገልግሎት በበኩር ጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ስለዚህ በስራው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበር /አ.ማ/ በአዲሱ አደረጃጀት የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የሚችሉ አጓጓዦች የማጓጓዣ ታሪፋችሁን በማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መሰረት በታሸገ ፖስታ በማቅረብ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::

 1. በዚህ የንግድ ዘርፍ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር/ቢሮ/የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድና የዘመኑን የመንግስት ግብር ሰለመክፈሉ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 2. የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት /ቲን/ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከ70 ኩንታል በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. እንዲሁም ተጫራቾች የሚያቀርቡት ከ70 ኩንታል በታች ከሆነ በክልል ትራንስፖርት ቢሮ ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፣
 5. የተሸከርካሪ ዝርዝር (ተ.ቁ፤የሰሌዳ ቁጥር፤ የመኪናው ዓይነት እና የመጫን አቅም) የሚያስረዳ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ወይም ከክልል መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ የተሰጠ የ2013 ዓ.ም. ወቅታዊ የታደሰ ምዝገባ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፣
 7.  ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ ይውላል:: የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሲሆን የሚከፈተው ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በዩኒየኑ ቢሮ ሲሆን መገኘት የማይችሉ ቢኖሩ ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም::ቅዳሜ እስከ 6፡30 የዩኒየኑ የስራ ቀን መሆኑ መታወቅ አለበት፣
 8. በዋጋ ማቅረቢያው ላይ የተጫራቾችን ስም እና አድራሻ በመጻፍ ለመርከብ ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ተብሎ በጉልህ ከተጻፈ በኋላ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ዩኒየኑ ለዚሁ ባዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ከመክፈቻው ቀን እና ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
 9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በፖስታ አሽጎ በመርከብ ዩኒየን ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 8፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ::
 10. የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥው በ20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊያንስ ይችላል::
 11.  ተጫራቾች ሁሉንም ቦታዎች ዋጋ መሙላት እና መወዳደር ይጠበቅባቸዋል::ማህበር መርጦ የሚወዳደር ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል::
 12. አሸናፊ የሚለየው በተናጠል ዋጋ ይሆናል::
 13.  ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ዝርዝር መረጃዎችን/የጨረታ ሰነድ/ የማይመለስ ብር 50 ሀምሳ ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር106 ማግኘት ይቻላል::
 14. ተወዳዳሪዎች በባንክ የተረጋገጠ 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ጥሬ ገንዘቡ በዩኒየኑ የገቢ ደረሰኝ ገቢ ተሰርቶ የገቢ ደረሰኙ ፎቶ ኮፒ ከላይ በተገለጹት በአንዱ የዋስትና አይነት አሰርተው ከፖስታው ውስጥ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
 15.  የጨረታው አሸናፊ በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት/5/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሸናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና አይነቶች የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት::
 16. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
 17. ስለ ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥው መነሻ ቦታ፤ ማራገፊያ ቦታ፤የሚጓጓዘው የሰብል ዓይነት ፤መጠን እና ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ይሆናል::

መርከብ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒየን ኃላ.የተ 1