Hamlin Fistula Ethiopia

Reporter Tir 19, 2013

ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን በጨረታ

ለመ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ፤ ቡራዩ፤ በታጠቅ/በደስታ መንደር/ የሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት/ መልሶ ማቋቋም ግቢ ውስጥ

 • ያገለገሉ መኪኖችን፣
 • ኮምፒውተሮችን
 • ስታብላይዘሮችን፣
 • የቤትና የቢሮ እቃዎችን
 • የህክምና እቃዎችን
 • የመኪና ስፔር ፓርቶች/መለዋወጫዎችን/
 • ያገለገሉ ባትሪና የመካከለኛ መኪና ጎማዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ህጋዊ ድርጅትም ሆነ ግለስብ በጨረታው ላይ ለመወዳደር የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ::

 1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
 2. ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ ከጦር ሃይሎች ወደ ወይራ በሚወስደው መንገድ አውግስታ ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ዋና /ቤት ፋይናንስ ክፍል በአማርኛ የተዘጋጀውን የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የማይመለስ ብር አንድ መቶ/100ብር/ እየከፈሉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ድረስዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ::
 3. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ታጠቅ/ደስታ መንደር/ በአዲሱ አምቦ መንገድ፤ ከአቢሲኒያ ባልትና 100 ሜትር አለፍ ብሎ ከዋናው መንገድ በስተግራ በሚያስገባው መንገድ 1 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ግቢ ውስጥ ከጥዋቱ 300 እስከ 1000 ሰዓት ድረስ ዘወትር ስኞ እሮብ እና አርብ በአካል መመልከት ይችላል::
 4. ተጫራቾች የሚገዙትን ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን የጨረታ መነሻ ዋጋ ሀያ በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እንዲሁም ሊገዙት ለሚፈልጉት ንብረት የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በድርጅቱ ግዥና ፍይናንስ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ/ለተመደበው ሰራተኛ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት /ማስረከብ ይኖርባቸዋል::
 5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው::
 6. ያገለገሉ ልዩ ልዩ ንብረቶችን የመነሻ ዋጋ ሀያ በመቶ (20%) ያልያስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል::
 7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
 8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን  ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 415 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ፍይናንስ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል:: ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል:: እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፣
 9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል:: ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፣
 10. ድርጅቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል::
 11. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
 12. ድርጅቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
 13. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0113-71 65 44/45/46  0112-60 11 53 0118-39 06 20 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል