• Wollo

Legehida Woreda Court

Addis Zemen Hidar 10, 2013

 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2013

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የለገሂዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ለመሥሪያ ቤቱ ሥራ አገልግሎት የሚውል ቀጥሎ የተዘረዘሩትን እቃዎች

 1. ኤሌክትሮኒክስ
 2. ልዩ ልዩ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎችና /የብረታ ብረት ሥራ እና ሌሎችም/
 3. የቢሮ አላቂ እቃዎች /የጽሕፈት መሳሪያዎች
 4. ልዩ ልዩ የህትመት ሥራዎች
 5. የደንብ ልብስ እና ተያያዥ ቁሳቁሶች
 6. ልዩ ልዩ የፅዳት እቃዎች
 7. ቋሚ አላቂ እቃዎች/ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በጨረታ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን /ቤቱ ይጋብዛል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
 4. የግዥው መጠን ብር 50.000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቪት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በደ//መስ/ዞን ለገሂዳ ወረዳ /ቤት ///አስ//የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% አንድ ፐርሰንት በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ደረቅ ቼክ ማስያዝ አይቻልም፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወጥ በሆኑ ቅጂ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ጠዋት 4:30 ድረስ በደ /ዞን ለገሂዳ ወረዳ /ቤት ///አስ// የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
 9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ይቆያል፡፡ በ16ኛው ቀን መጨረሻ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ ወዲያውኑ ከጠዋቱ 500 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ በይፋ ይከፈታል፡፡
 10. ማንኛውም አሸናፊ ተጫራች እቃዎችን ርክክብ ሲፈጽም ጥራቱ በባለሙያ ተረጋግጦ የታሸጉ እቃዎች ተፈተውና ታይተው፣ ተቆጥረው፣ ተለከተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ከሆነ 5 ቀናት ውስጥ መልሶ መተካት ይኖርበታል፡፡
 11. ተጫራቾች በሚሞሉት የእቃ ዋጋ ላይ መለኪያና ጥራቱን ጠብቀው መሙላትና ማቅረብ አለባቸው፡፡
 12. የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት መወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ሆኖ በውለታ ሰነዱ ላይ በዝርዝር ይቀመጣል፡፡
 13. ከአሽናፊ ተጫራቾች 2%/ ሁለት ፐርሰንት / ከ10,000.00 ብር በላይ ግዥ ሲፈፀም ዊዝ/ ሆልዲንግ ግብር  ይሰበሰባል፡፡
 14. /ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ በጥቅልም ሆነ በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 15. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 16. ተጫራቾች ተራ ቁጥር 1.23 እና 4 ለእያንዳንቸው 20/ሃያ ብር/ ተራ ቁጥር 5.6 እና 7 ለእያንዳንዳቸው 15 /አስራ አምስት ብር/ በመከፈል ከደ//ዞን ለገሂዳ ወረዳ /ቤት // አሰ//የስራ ሂደት ድረስ በማቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
 17. አንድ ተጫራች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይችልም፡፡ ሆኖም በሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት እቃዎች ውስጥ አንድ እቃ ዋጋ ሳይሞላበት ቢቀር ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
 18. መሥሪያ ቤቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በሎት ነው፡፡
 19. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርብላቸው የተጠየቁ እቃዎች ካሉ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ወይም ጨረታው በሚጠናቀቅበት ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 20. አሸናፊ የሆነ አካል የእቃ ርክከቡን የሚፈፅመው በደቡብ ወሎ ዞን በለገሂዳ ወረዳ ፍርድ ቤት ነው፡፡
 21.  ውል የሚወስደውም በዚሁ ወረዳ ፍትሕ /ቤት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 22.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0332412001 ወይም 0927412789 / በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ደቡብ ወሎ ዞን ከፍ//ቤት ለገሂዳ ወረዳ /ቤት

ለገሂዳ