Hope for Justice Ethiopia

Addis Zemen Tir 26, 2013

ክፍት የጨረታ ማስታወቂያ

ሆፕ ፎር ጀስቲስ ኢትዮጵያ መንግሥታዊ ያልሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራባቸው አበይት ጉዳዮች መካከል በተለያየ ምክንያት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ለተለያየ ችግር እና ብዝበዛ የተጋለጡ ሕፃናትን ወደማቆያ ማዕከላችን በማስገባት የስነልቦና ድጋፍ፣ የህይወት ክህሎት ስልጠና፣ የመጠለያ፣ የአልባሳት እንዲሁም የህክምና አገልግሎት በመስጠት ከቤተሰባቸው ጋር እንዲዋሃዱ ወይም በቋሚነት ከማህረሰቡ ጋር እንዲቀላቀሉ ማድረግ ነው።

ድርጅታችን ለዚህ ሥራ ይረዳን ዘንድ ከታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት የመኪናዎች ለአንድ ዓመት ኮንትራት ለመከራየት ተዘጋጅተናል፡፡

መስፈርቶች:

 1. .. 2007 ዓመት በኋላ የተመረቱ መኪናዎች፤
 2. የግብር ከፋይ የኢንሹራንስ እና ሦስተኛ ወገን እና ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማቅረብ የሚችሉ፤
 3. በጥሩ ይዞታ ላይ የሚገኙና ብልሽት የሌላቸውን መኪናዎች ማቅረብ የሚችሉ፤
 4. በተፈለገ ጊዜ ሁሉ ለድርጅታችን መኪና ማቅረብ የሚችሉ/ በተጠየቁ በሁለት ሰዓት ማቅረብ የሚችሉ፤
 5. መኪናዎቹ ሁሉ የመጀመሪያ ዕርዳታ ቁሳቁስ ያላቸው፤
 6. አራት ሰው በላይ መጫን የሚችሉ፤
 7. ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች እና የገጠሪቱ ክፍል ለመሄድ ፍቃደኛ የሆኑ፤
 8. በጉዞ ወቅት መኪናው እክል ሲያጋጥመው ሌላ መኪና ወደ ቦታው በመላክ/ በመተካት ሥራውን ማስኬድ የሚችሉ፤
 9. አስፋልት እና ጠጠር መንገድን ግምት ውስጥ ያስገባ ሂሳብ ማቅረብ የሚችሉ፤
 10. ሹፌሮቹ የድርጅታችንን የሕፃናት ጥበቃ ስልጠና ለመውሰድ ፍቃደኛ የሚሆን፤
 11. ሹፌሮቹ ከወንጀል ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጫ ማምጣት የሚችሉ፤
 12. ሹፌሮቹ የደህንነትና የጥንቃቄ አነዳድ ስልጠና የወሰዱ፤
 13. በእያንዳንዱ ጉዞ ለድርጅታችን ሎግ ሺት ማቅረብ የሚችሉ፤
 14. የሁለት ወር የሙከራ ጊዜ ግምገማ በኋላ አንድ ዓመት ኮንትራት መግባት የሚችሉ፤
 15. በተመሳሳይ ሥራ /ከተመሳሳይ ድርጅት ጋር መሰማራታቸውን የሚገልጽ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ በወጣ ሰባት የሥራ ቀናት የተሟላ ዶክመንታቸውን በሆፕ ፎር ጀስቲስ ዋና ቢሮ EGST ሕንፃ 2 ፎቅ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0911542399 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጥር 24/2013 ነው፡፡

ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡

ሆፕ ፎር ጀስቲስ ኢትዮጵያ